አልማዝ ባለጭራ – Herpes zoster

በግማሽ የሰውነት ክፍል ላይ በድንገት የሚወጣ ሽፍታ ሲሆን ብዙዉን ጊዜ ሽፍታው መስመር ይዞ ውኃ ቋጥሮ በጣም የሚያም ነው፡፡ በየትኛዉም የሰዉነት ክፍል ላይ ሊወጣ ይችላል አብዛኛውን ጊዜ ግን በጀርባ፣ በማጅራት፣ በደረት ወይም በፊት ላይ ይወጣል፡፡ በአገራችን አባባሉ ሳይንሳዊ መሰረት ባይኖረውም አልማዝ ባለጭራ እየተባለ ይጠራል::
የአልማዝ ባለጭራ በሽታ ዋና መንስኤ ጉድፍን የሚያስከትለው ቫሪሴላ ዞስተር ቫይረስ (Varicella Zoster Virus) ነው ፡፡ ህመሙ ምንም እንኳን ለህልፈተ ህይወት ባይዳርግም ከፍተኛ ስቃይ/ህመም ሊያመጣ ይችላል፡፡

የህመሙ ምልክቶች
-ብዙዉን ጊዜ በአንዱ የሰዉነት ክፍል በኩል/በቀኝ ወይም በግራ በኩል/ የሚታይ ነዉ፡፡
– የማቃጠል፣ ማሳከክ
-የመደንዘዝ ወይም መጠቅጠቅ ህመም
-የጡንቻ ህመም (ድካም)
-ህመሙ ከተከሰተ ከጢቂት ቀናት በኃላ ቀይ ሽፍታ መከሰት/መጀመር
-ትኩሳት
-የራስ ምታት የመሳሰሉት ናቸው
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
-ከዚህ በፊት ጉድፍ የነበረባቸውን ሰዎች
-የተወሰኑ የህመም አይነቶች እንደ ካንሰር፣ ኤች አይቪ፣ ስኳርና ሌሎች የሰዉነትን የበሽታ መከላከል አቅም የሚቀንሱ ህመሞች ካሉ
-እድሜ ከ50 ዓመታትና ከዚያ በላይ ሲሆን
መፍትሄ
-ወደ ቆዳና አባለዘር ሐኪም መሄድ
-ሕክምናው ከሐኪም ጋር በመነጋገር የሚካሄድ ሲሆን የተለያዩ አማራጮች ያሉት ነው፤የአልማዝ ባለጭራ (ኸርፐስ) በቫይረስ አማካኝነት የሚከሰት እንደመሆኑ ጨርሶ ከሰዉነት ዉስጥ የሚያስወጣ መድሃኒት የለም ቢሆንም አንዳንድ ሁኔታውን ለማቅለል የሚታዘዙ የፀረ ቫይረስ መድኃኒቶች አሉ ፡፡ በአፍም ሆነ በቅባት መልክ የሚወሰዱ መድኃኒቶች ቁስሉ ወዲያው እንደጀመረ ቶሎ መወሰድ አለባቸው፤ በፍጥነት ለማገገም ይረዳሉ፡፡
በተጨማሪም – ህመምና ሽፍታ በአይን ዙሪያ ከወጣ ይህ አይነት እንፌክሽን ካልታከመ የማይመለስ ጉዳት በአይን ላይ ሊያመጣ ይችላል፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.