Experts View of The Diaspora Trust Fund Account | የትረስት ፈንድ ሃሳብ በዲያስፖራው እና በባለሙያዎች ዕይታ

ከሁለት ሳምንት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የ2011 ዓ.ም ረቂቅ በጀትን በሙሉ ድምፅ ባፀደቀበት ስብሰባ ላይ አዲስ ምክረ-ሃሳብ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለአገር እድገት ይበጃል ያሉት ይህ ምክረ-ሃሳብ፤ የትረስት ፈንድ ማቋቋምን ይመለከታል። ”በቦርድ የሚመራ እና ወጪ እና ገቢው በትክክል የሚታወቅ ‘ትረስት ፈንድ’ በማቋቋም ዲያስፖራው በየቀኑ አንድ ዶላር እንዲለግስ እንጠይቃለን” ብለዋል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አገሪቱ ቢያንስ በየቀኑ 1 ሚሊየን ዶላር ልታገኝ እንድምትችል ተስፋ አድርገዋል።

• ዶላር በጥቁር ገበያ ለምን ቀነሰ?

• ኢትዮጵያ በዱቤ ተጨማሪ ነዳጅ ከሳኡዲ አረቢያ ጠየቀች

ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገር ቤት የሚልኩት ገንዘብ ህጋዊ መንገድን የተከተለ በማድረግ ”ህገ-ወጥነትን በመከላከል አገራችሁን ጥቀሙ” ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ነበር።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውጡን ለማደናቀፍ የሚሞክሩትን አስጠነቀቁ

ትረስት ፈንድ ምንድነው?

ትረስት ፈንድ ህጋዊ አካል የሆነ ለግለሰቦች፣ ለቡድን ወይም ለድርጅት ጥሬ ገንዘብን ወይም ንብረትን የሚያስተዳድር ፍንድ ማለት ነው።

የተለያዩ የትረስት ፈነድ አይነቶች ያሉ ቢሆንም ሁሉም ሦስት ተመሳሳይ መሰረታዊ ይዘት አላቸው። እነዚህም ጥሬ ገንዘብ ወይም ንብረትን የሚለግስ፣ የሚያስተዳድር እና የፈንዱ ተጠቃሚ አካላት ናቸው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃሳብ መሰረት የሚቋቋመው ትረስት ፈንድ መቀመጫውን በኢትዮጵያ ወይም ከኢትዮጵያ ውጪ ያደርጋል። ከዚያም ፍቃደኛ የሆኑ የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በተወሰነ የጊዜ ልዩነት ለትረስት ፈንዱ መዋጮ ይፈጽማሉ።

• “ለዋጋ ግሽበት የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያው ምክንያት ነው”

• የብር የመግዛት አቅም መቀነስ አንድምታዎች

ከሁለት ቀናት በፊት የትረስት ፈንዱ የሂሳብ ቁጥር ይፋ የተደረገ ሲሆን ፍቃደኛ የዲያስፖራ አባላት በቅርቡ ይፋ በሚደረገው የትረስት ፈንዱ ድረ-ገጽ አሊያም ወደ 22 የሚጠጉ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶችን በመጠቀም ገንዘብ ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ሃሳብ ይፋ ሲያደርጉ ”ዲያስፖራዎች ለአንድ ማኪያቶ እሰከ 5 ዶላር ድረስ ያወጣሉ። ከማኪያቶ ወጪያቸው ላይ ለአገራቸው 1 ዶላር በየቀኑ ቢያዋጡ በወር 30 ሚሊዮን ዶላር ለኢትዮጵያ ያስገኛል ማለት ነው” ብለዋል።

የዲያስፖራው አንድ ዶላር

ዲያስፖራው ምን ይላ?

አቶ ሃብታሙ አበበ አሜሪካን አገር ሜሪላንድ ግዛት ውስጥ ይኖራሉ። ”በእድሜዬ በኢትዮጵያ ውስጥ አያለው ብዬ ያላሰብኩትን አይነት ለውጥ እየታዘብኩ ነው። በዚህም በጣም ደስተኛ ነኝ፤ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ” ይላሉ።

አቶ ሃብታሙ ጨምረውም ”ጠቅላይ ሚንስትሩ የዲያስፖራው አስተዋጽኦ ምን መሆን እንዳለበት በትክክል አስቀምጠዋል፤ እኔም ሆንኩ ባለቤቴ ትረስት ፈንዱ ተቋቁሞ ግዴታችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን” ሲሉ ሃሳባቸውን አጋርተውናል።

በሌላ በኩል ነዋሪነታቸውን በእንግሊዝ አገር ያደረጉት አቶ ጳውሎስ አያሌው ”ያለምንም ዲሞክራሲ እና የህግ የበላይነት ሲመራ የቆየ መንግሥት አሁን ፊቱን አዙሮ ገንዘብ አዋጡ ማለቱ ለእኔ ታዓማኒነት የለውም። ከውጪ የሚመጣውን ገንዘብ የማስተዳደሩ አቅም የላቸውም፤ ህዝብም አልመረጣቸውም። አንዲያውም በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ሙስና ከማባባስ ውጪ ለህዝቡ ፋይዳ አይኖረውም” በማለት ትረስት ፈንድ የማቋቋም ሃሳቡን አጣጥለዋል።

በተቃራኒው ደግሞ ነዋሪነቷን በአሜሪካን አገር ቨርጂኒያ ግዛት ያደረገችው ፀደይ ብዙአየሁ ”ጠቅላይ ሚንስትሩ ያሉትን ለመፈጸም በጣም ዝግጁ ነኝ፤ እኔ የምፈልገው እኛን የሚወክሉ ግለሰቦች የትረስት ፈንዱ አካል ሆነው አፈጻጸሙን የሚያሳዩ ወቅታዊ የሆኑ ሪፖርቶችን እንዲያደርሱን ብቻ ነው” ትላለች።

በአሜሪካን አገር ሚኒሶታ ግዛት የሚኖረው እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆነው ያሬድ ገብረወልድ የጠቅላይ ሚንስትሩን ሃሳብ በአዎንታዊ መልኩ ይቀበላል። ”ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን ሃሳብ ከማንሳታቸው በፊትም አገራችንን አንዴት መርዳት እንዳለብን በቤተሰብ ደረጃ የምንወያይበት ርዕሰ ጉዳይ ነው” ይላል።

ያሬድ ጨምሮም ”በርካታ ሰው አገሩን በገንዘብ መርዳት ይፈልጋል ይሁን እንጂ የሚያዋጣው ገንዘብ ለጦር መሳሪያ ግዢ ይውላል፣ የሙሰኞች ሲሳይ ይሆናል የሚሉ ስጋቶች ናቸው ከመለገስ እንድንቆጠብ የሚያደርጉን። ተጠያቂነት እና ግልፅነት የሰፈነበት አሰራር ካለ የሚጠበቅብንን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነን” ብሏል።

የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይታ

የቀድሞ የአዲስ አበባ እና የኢትዮጰያ ንግድ ምክር ቤቶች ፕሬዝዳንት የነበሩት እና የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ክቡር ገና የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳብ የሚዋጥላቸው አይመስልም። አቶ ክቡር ”የትረስት ፈንድን የማቋቋም ሃሳብ ከውጪ የሚመጣውን ገዘንብ አጠናክሮ ከማስቀጠል ያለፈ ሌላ ፋይዳ አይኖረውም” ይላሉ።

”ስለ ትልቅ ገንዘብ ነው እያወራን ያለነው። ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚሉትን አይነት ገንዘብ ከማኪያቶ ወጪ ላይ በመቆጠብ የሚመጣ አይነት አይደለም። አሁን በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የፋይናንስ ቀውስ ለመቅረፍ ታስቦ የመጣ ሃሳብ ከሆነ፤ ይህ ሃሳብ የሚያስኬድ ስላልሆነ እንደገና ቢታሰብበት እለላሁ” ሲሉ ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።

አቶ ክቡር ”በግሌ በዲያስፖራ አላምንም። ዲያስፖራው በአገሪቱ ምጣኔ ሃብት ላይ የራሱ አስተዋጽኦ እንዳለው እገነዘባለሁ። ይሁን እንጂ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው አገር ውስጥ ላለው ሃብት ነው” በማለት ሃሳባቸውን ያጠናክራሉ።

ሌላው የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ኑሩ ሰይድ (ዶ/ር) ግን የዲያስፖራውን አቅም ሲያስረዱ ”ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገሪቱ የሚልኩት የገንዘብ መጠን አገሪቱ ወደ ውጪ ነግዳ ከምታገኘው በሁለት እጥፍ ይበልጣል” ይላሉ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የዲያስፖራውን አቅም ስለሚረዱ ነው ይህን አይነት ጥሪ ያደረጉት የሚሉት ዶ/ር ኑሩ ”ከዚህ በፊት መንግሥትን ለመጉዳት ታስቦ ዲያስፖራው ወደ አገር ውስጥ ዶላር እንዳይልክ የተለያዩ ቅስቀሳዎች ይደረጉ ነበር፤ እንዲሁም ህጋዊ መንገዶችን ባልተከተለ መልኩ ገንዘብ ወደ አገር ውስጥ እንዲገባ ይደረግ ነበር። አሁን ግን የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃሳብ ይህን እንኳን ማስቀረት የሚያስችል ከሆነ አገሪቱ በእጅጉ ልትጠቀም ትችላለች” ይላሉ።

ነገር ግን ዶ/ር ኑሩም ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚሉትን የገንዘብ መጠን በትረስት ፈንዱ በኩል ማግኘት ቀላል ሊሆንላቸው አይችልም ይላሉ። ”ይህ ሃሳብ በየትኛውም አቅጣጫ የሚገኘውን የዲያስፖራ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለማግኘት የተደረገ የቅስቀሳ አካል አድርጌ ነው የምመለከተው እንጂ እሳቸው የሚሉትን ያክል ገንዘብ ከዲያስፖራው ለመሰብሰብ የሚቻል አይደለም” በማለት ሃሳባቸውን ይሰነዝራሉ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

17 Comments

  1. Thanks for some other wonderful article. The place
    else could anybody get that kind of information in such
    an ideal means of writing? I have a presentation next
    week, and I am at the look for such info.

  2. Hi there, just became aware of your blog through Google,
    and found that it is truly informative. I’m going to watch out for brussels.
    I’ll appreciate if you continue this in future. Lots
    of people will be benefited from your writing. Cheers! 34pIoq5 cheap flights

  3. Hey there terrific website! Does running a blog similar
    to this require a large amount of work? I’ve virtually no knowledge
    of coding however I had been hoping to start my own blog soon. Anyway, should you have any suggestions or tips for new
    blog owners please share. I know this is off subject but
    I just needed to ask. Cheers! cheap flights 3aN8IMa

  4. I’m no longer sure where you’re getting your information, however great topic.

    I must spend some time learning much more or
    figuring out more. Thanks for fantastic info I used to be
    searching for this information for my mission. cheap
    flights 3aN8IMa

  5. Have you ever thought about creating an ebook or guest authoring on other sites?
    I have a blog centered on the same subjects you discuss and would love to have you
    share some stories/information. I know my readers would value your
    work. If you are even remotely interested, feel free to send me an e mail.

  6. Hey would you mind stating which blog platform you’re using?
    I’m going to start my own blog soon but I’m having a hard time selecting between BlogEngine/Wordpress/B2evolution and Drupal.
    The reason I ask is because your layout seems different then most blogs and I’m looking for something completely unique.
    P.S Sorry for being off-topic but I had to ask!

  7. I’m impressed, I have to admit. Seldom do I come across a blog that’s equally educative and interesting, and
    without a doubt, you have hit the nail on the head.

    The issue is something which not enough men and women are
    speaking intelligently about. Now i’m very happy
    I came across this in my search for something concerning this.

  8. Thanks for finally talking about > Experts View of The Diaspora Trust Fund Account |
    የትረስት ፈንድ ሃሳብ በዲያስፖራው እና በባለሙያዎች ዕይታ –
    መጽሔት < Liked it!

Comments are closed.