በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል መቼ ምን ተከሰተ?

የኢትዮጵያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያልተጠበቀ ውሳኔ ከኤርትራ ጋር ለዓመታት የዘለቀውን ቀዝቀቃዛ ጦርነት ሊያበቃ እንደሚችል ተስፋ ሰጥቷል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በሚያዚያ 28/1990 ዓ.ም ነበር የድንበር ጦርነቱ የተጀመረው።

ምንም እንኳ በታህሳስ 2002 ዓ.ም የሁለቱ ሃገራት መሪዎች አልጀርስ ላይ ከሰላም ስምምነት ቢደርሱም፤ የአገራቱ ሠራዊት ድንበር ላይ ለጦርነት በተጠንቀቅ እንደተፋጠጠ ይገኛሉ።

ግንቦት 28 2010 ዓ.ም የኢህአዴግ ስራ እፈጻሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም ለረዥም ዓመታት በሁለቱ አገራት መካካል ቆይቶ የነበረውን ሰላምም ሆነ ጦርነት የሌለበትን ውጥረት ሊቀይር ይችላል የሚል ተስፋን ሰንቋል።

የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ኢኮኖሚያዊ ትርፍ?

ኢትዮጵያና ኤርትራ የት ድረስ አብረው ይራመዳሉ?

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ በህዝብ እንደራሴው ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር ሲያደርጉ ፍጥጫው ሠላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ ጥሪ ቢያቀርቡም በወቅቱ ከኤርትራ በኩል የተሰጠው ምላሽ ጥሪው ቀደም ያሉት የኢትዮጵያ መሪዎች ካቀረቡት የተለየ አለመሆኑን በመጥቀስ ውድቅ አድርገውታል።

ኢትዮጵያ የአልጀርስ ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እተገብራለሁ ማለቷን ተከትሎ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አንድ የልዑካን ቡድን ወደ አዲስአበባ እንደሚልኩ ገልፀዋል።

“ኢትዮጵያውያን ከኤርትራውያን ጎረቤቶቻቸው ጋር በሰላም መኖር ይሻሉ” ብለዋል ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ።

ፕሬዚዳንቱ ይህንን ያሉት የሰማዕታት ቀንን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር ሲሆን ጉዳዩን በቀጥታና በጥልቀት ለማወቅና ቀጣይ የስራ እቅድ ለማውጣት እንደሆነም ጨምረው ተናግረዋል።

የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት 20ኛ ዓመት - መቋጫ ያላገኘ ፍጥጫImage copyrightALEXANDER JOE

ኢትዮጵያና ኤርትራ ቁልፍ ክንውኖች- የጊዜ ሰሌዳ

ግንቦት 16፣ 1985 ኤርትራ ከኢትዮጵያ ነጻ መውጣቷን በሕዝበ ውሳኔ አሳወቀች

ሚያዚያ 28፣ 1990- ደም አፋሳሹ የድንበር ጦርነት ተጀመረ።

ከ1990-1992- ሁለቱ አገራት ደም አፋሳሽ የድንበር ጦርነት አደረጉ። ከሰባ ሺ በላይ ዜጎች ሞቱ።

ሰኔ፣ 11 1992- ሁለቱ አገራት በጠላትነት ላለመተያየት ሰነድ ፈረሙ

ታኅሳስ 03/1993 የአልጀርስ የሰላም ስምምነት ተፈረመ

ሚያዚያ 05/1994 የኢትዮ-የኤርትራ ድንበር ኮሚሽን ይግባኝ የሌለውን ውሳኔ አሳወቀ።

ጥር፣ 1994- የኤርትራ ብሔራዊ ሸንጎ ማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ምዝገባ እንዳይካሄድ አገደ።

ኅዳር 1998 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱ አገራት ወደ ሰላም ካልተመለሱ ማዕቀብ እንደሚጥል አሳወቀ።

ኅዳር 1998- ኤርትራ አሜሪካዊያንን አውሮፓዊያንና ራሻዊያን ያሉበትን የሰላም አስከባሪ ከድንበር አባረረች።

መጋቢት 1999-ኤርትራ ራሷን ከምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) አገለለች።

ኅዳር 2002-የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤርትራ በሶማሊያ አክራሪዎችን ታስታጥቃለች በሚል ማዕቀበል ጣለ።

መጋቢት 2003- ኢትዮጵያ ለኢሳያስ መንግስት ተቀናቃኞች እርዳታ እንደምትሰጥ አሳወቀች

ታኅሳስ 2004- ኢትዯጵያ ኤርትራ አፋር ድንበር ላይ ቱሪስቶችን ገድላለች ስትል ከሰሰች

የካቲት፣ 2004 ኤርትራ የኢትዮጵያ አማጽዮችን ለማሰልጠን ኤርትራ ትጠቀምበታለች የሚባለውንና በደቡብ ምዕራብ ኤርትራ የሚገኘውን ወታደራዊ ካምፕ አጠቃች።

ነሐሴ፣ 2004- መለስ ዜናዊ ከሃያ ሁለት ዓመታት የሥልጣን ቆይታ በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ታኅሳስ፣ 2005- የተቃዋሚ ወታደሮች በአስመራ የሚገኘውን የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሕንፃ ተቆጣጠሩ።

ግንቦት 2007- የኤርትራ መንግሥት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ይፈጽማል ሲል የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት ወቀሰ።

ሰኔ፣ 2008- ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ኤርትራ የምታደርገውን የወታደራዊ ቆስቋሽነት እንድታስታግስ፥ ይህ ካልሆነ ግን ወታደራዊ ጥቃት እንደሚሰነዘሩ አሳሰቡ።

ነሐሴ፣ 2008- ኢትዮጵያና ኤርትራ በፆረና ግምባር ጦርነት አደረጉ፤ አንድ መቶ ወታደሮች ተገደሉ።

ግንቦት፣ 2009- የኳታር ሰላም ጠባቂዎች ከድንበር አካባቢ መውጣታቸውን ተከትሎ በጅቡቲና ኤርትራ መሐል ውጥረት እንዲነግስ ሆነ።

መስከረም፣ 2010- የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሊህ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ኃላፊዎችን ከጦርነቱ መልስ ለመጀመርያ ጊዜ አግኝተው ተወያዩ።

መጋቢት 24፣ 2010- ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሐላ ፈጸሙ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.