SPORT NEWS: WORLD CUP 2018 Begins Today | የ2018 የዓለም ዋንጫ ዛሬ ይጀመራል

በሙለታ መንገሻ

በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2018 የፊፋ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ዛሬ መካሄድ ይጀምራል።

የዓለም ዋንጫው በምደብ አንድ የሚገኙት በአስተናጋጇ ሩሲያ እና ሳዑዱ አረቢያ መካከል በሉዝህኒዝኪ ስታዲየም በሚደረግ ጨዋታ ነው የሚጀመረው።

በ21ኛው የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ላይ 32 ሀገራት የሚፋለሙ ሲሆን፥ በ32 ቀናት ቆይታም 64 ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።

በሩሲያ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2018 የፊፋ የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ጨዋታዎች በሩሲያ በሚገኙ 11 ከተሞች በተዘጋጁ 12 ስታዲየሞች ውስጥ ነው የሚካሄዱት።

በዘንድሮው የዓለም ዋንጫም የ2014 የዓለም ዋንጫ ያሸነፈችው ጀርመን የሩሲያን የዓለም ዋንጫ በማንሳት በአውሮፓውያኑ ከ1962 ወዲህ የዓለም ዋንጫን ለሁለት ተከታታይ ጊዜ ያነሳች ሀገር የመሆን ተስፋን ሰንቃለች።

ብራዚል ደግሞ የዘንድሮውን የዓለም ዋንጫ በማንሳት ያሸነፈቻቸውን የዓለም ዋንጫ ብዛት ወደ ስድስት በማሳደት ክብረ ወሰኗል ለማስጠበቅ አቅዳለች።

የ20ኛው የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን፣ የ5 ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸናፊ ብራዚል፣ የ2016 የአውሮፓ ዋንጫ አሸናፊዋ ፖቹጋል፣ የ2014 ዓለም ዋንጫ ለፍፃሜ የደረሰችው አርጀንቲና እንዲሁም ቤልጂየም፣ ፖላንድ እና ፈረንሳይ የዓለም ዋንጫውን የማንሳት ቅድመ ግምት የተሰጣቸው ሀገራት ሆነዋል።

አስተናጋጇ ሩሲያ በፊፋ ወርሃዊ የሀገራት የእግር ኳስ ሰንጠረዥ ምንም እንኳ ከዓለም 70ኛ ደረጃ ላይ ብትቀመጥም የዓለም ዋንጫውን ሀገሯ ላይ ልታስቀር ትችላለች የሚል ግምትም ተሰጥቷታል።

በመጨረሻ ሰዓት አሰልጣኟን ያባረረቸው ስፔን እና ከ8 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ አንዱን ብቻ ማሳካት የቻለችው እንግሊዝም ከሌሎቹ ሀገራት በመቀጠል ግምት ውስጥ ገብተዋል።

በዘንድሮው የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ላይ ፓናማ እና አይስላንድ የዓለም ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዋቸውን የሚያደርጉ ሀገራትም ናቸው።

አጠቃላይ የህዝብ ቁጥሯ 335 ሺህ የሆነችው አይስላንድ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ትንሽ የህብዝ ቁጥር ያላት የመጀመሪያዋ ተሳታፊ ሀገር መሆንም ችላለች።

ፓናማም በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓለም ዋንጫ ባለፈችበት ጊዜ በሀገሪቱ ብሄራዊ በዓል ታውጆ ተከብሮ እንደነበረም አይዘነጋም።

በአጠቃላይ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ላይ 32 ሀገራት በስምንት ምድብ ተከፋፍለው የሚፋለሙ ሲሆን፥ አሸናፊው ሀገርም እሁድ ሀምሌ 8 2010 ዓ.ም 81 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም ባለው በሉዝህኒዝኪ ስታዲየም በሚደረግ ጨዋታ ይለያል።

የ2018 የዓለም ዋንጫ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ደጋፊዎች ወደ ሩሲያ በመጓዝ እንደሚመለከቱት ይጠበቃል።

በተጨማሪም በመላው ዓለም ላይ ከ3 ቢሊየን በላይ ሰዎች በቴሌቪዥን መስኮት የ2018 የሩሲያ ዓለም ዋንጫን ባሉበት ሆነው እንደሚከታተሉም ተገምቷል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

Advertisement

14 Comments

  1. Does your blog have a contact page? I’m having problems locating it
    but, I’d like to send you an e-mail. I’ve got some suggestions for your blog you might be interested in hearing.

    Either way, great blog and I look forward to seeing it improve
    over time.

  2. I really like what you guys are up too. This sort of clever work and reporting!
    Keep up the terrific works guys I’ve included you guys to blogroll.

    yynxznuh cheap flights

  3. My partner and I stumbled over here coming from a different page and thought I might check things out.

    I like what I see so now i am following you. Look forward to looking over your web
    page for a second time. 3aN8IMa cheap flights

  4. Hey would you mind stating which blog platform you’re using?

    I’m looking to start my own blog soon but I’m having a hard time deciding between BlogEngine/Wordpress/B2evolution and Drupal.

    The reason I ask is because your layout seems different then most
    blogs and I’m looking for something completely unique.
    P.S Apologies for being off-topic but I had to ask!
    y2yxvvfw cheap flights

  5. Right now it appears like Expression Engine is the top blogging platform
    available right now. (from what I’ve read) Is that what you’re using on your blog?

Comments are closed.