የደም ካንሰርና ምልክቶቹ – Signs For Leukemia

የደም ካንሰር (leukemia) የደም ህዋሶችን የሚያጠቃ አንድ የካንሰር በሽታ አይነት ነው። የደም ካንሰር በሚከሰትበት ጊዜ ከተለምዶ ወጣ ያሉ (abnormal) የደም ሴሎች በመቅኒ (bone marrow) ውስጥ ይመረታሉ። አብዘሃኛውን ጊዜ እነዚህ የሚመረቱት የደም ሴሎች በሽታን ለመከላከል የሚጠቅሙን ነጭ የደም ሴሎች ናቸው።
ታዲያ እነዚህ ለየት ብለው የሚመረቱ ነጭ የደም ሴሎች ዋናዎቹ የደም ሴሎች እንደሚሰሩት አይሰሩም። እልቁንስ ህዋሶቹ በማደግና በመከፋፈል ጤናማ የሆኑትን ነጭ የደም ሴሎች በመክበብ ያጨናንቃሉ። በስተመጨረሻም ሰውነታችን በሽታን መከላከል፣ የደም መፍሰስን ማቆም እና አየርን በቀላሉ ወደ ተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ማስተላለፍ ያቅተዋል።
የደም ካንሰር ምልክቶች
የደም ካንሰር ምልክቶች እንደ በሽታው አይነት ይለያያሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ ዋና የደም ካንሰር ምልክቶች የሚከተሉትን ይመስላሉ።
ትኩሳት ወይም ማንቀጥቀጥ
ከየት መጣ የማይባል የሁልጊዜ ድክመት
ተደጋጋሚ ወይም ከፍተኛ ኢንፌክሽን
ምንም ሳይሞክሩ የሚከሰት የክብደት መቀነስ
በቀላሉ የደም መፍሰስ
ተደጋግሞ የሚመጣ ነስር
በቆዳ ላይ የሚከሰቱ ትንንሽ ቀያይ ምልክቶች
ከመጠን በላይ የሆነ ላብ በተለይ በምሽት ጊዜ
የአጥንት ሕመም
ዶክተር መች ማየት አለብን?
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች በተደጋጋሚ ሲከሰቱ ወይም ደግሞ የሚያስጨንቀን ምልክት ካየን በአስቸኳይ ወደሚመለከተው ዶክተር በመሄድ መታየት ይኖርብናል። የደም ካንሰር ምልክቶች ብዙውን ጊዜ ግልጽ እና ቀጥተኛ ሆነው አይገኙም። የመጀመሪያ የደም ካንሰር ምልክቶችን ከጉንፋን ወይም ከሌሎች ቀላል በሽታዎች ጋር በማመሣሰል የሚያስፈልገውን ሕክምና ሳናገኝ ልንጎዳ እንችላላን።

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.