የስኳር አወሳሰዳችንን እንድንቀንስ የሚያስገድዱን ምክንያቶች

አብዛኛውን ጊዜ ከተፈጥሮ ውጪ ማዕዳችን ላይ ከምናገኛቸው ምግቦችና መጠጦች መካከል ለስላሳ መጠጦች፣ኬኮች፣የወተት ተዋፅዖች እና ሌሎችም ይገኛሉ፡፡
የስኳር ይዘት ያላቸው ምግቦችና መጠጦች በባህሪያቸው ካሎሪ የላቸውም እንዲሁም ከፋብሪካ ኬሚካላዊ ሂደት ጠብቀው የሚመረተው ስኳር ደግሞ ምንም ዓይነት ቪታሚን፣ ንጥረ-ነገር፣ ፕሮቲን፣ ፋይበር እና ሌሎች ለሰው ልጅ የሚስፈልጉ ጠቃሚ ነገሮችን የለውም ይላሉ፡፡

1.ለውፍረት ያጋልጣል
በተለያዩ ወቅቶች የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ በተለይም የስኳር ይዘት ያለቸው መጠጦች ለውፍረት እንደሚያጋልጡን ያሳያሉ፡፡
ይህ የሚሆነው ስኳር ካሎሪ ስለሌለው ሰውነታችን ስብን እንዳያቃጥል ስለሚያደርገው ነው ይላሉ በዚህም የምግብ መፈጨት ሂደትን ያዛባል የረሃብ ስሜታችንን በማነሳሳት ብዙ እንድንመገብም ያደርገናል ይላሉ ጥናቶች፡፡

2.በዓይነት ሁለት የስኳር ዓይነት የመያዝ እድልን ያሰፋል
የበዛ የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦች በጉበት አካባቢ ስብ እንዲከማች ያደርጋሉ ቀስ በቀስ የጣፊያን ተግባር ማወክ ይጀምራሉ፡፡
የጉበት ችግር ያስከትላል
ይህም በተመሳሳይ ባልተመጠነ ስኳር አወሳሰድ የሚከሰት ችግር ሲሆን፥ የበዛ አወሳሰድ በጉበት ላይ ከፍተኛ የስራ ጫና በመፍጠር መደበኛ የሆነውን ተግባሩን ያውካል በዚህም ጉበት ላይ ችግር ይከሰታል፡፡

3.ልብን ያደክማል
በስኳር ውስጥ ያለው ፍሩክቶስ መልካም ያልሆነ ኮሌስትሮል በሰውነታችን ውስጥ እንዲከሰት ያደርጋል እንዲሁም የደም ቧንቧዎች ላይ እክል ይፈጥራል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ ሰውነታችን ላይ የኢንሱሊን መጠን ይጨምራል በዚህም የደም ግፊትና የልብ ምት እንዲጨምር ምክንያት ይሆናል፡፡

4.ጭንቀትና ድብርት ያስከትላል
አዕምሮ መደበኛ ስራውን ለመስራት ግሉኮስና ኢንሱሊን ይፈልጋል ሆኖም ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦችንና መጠጦችን
አንድ ሰው ከተጠቀመ ከፍተኛ የሆነ የግሉኮስና የኢንሱሊን ምርት ወደ አዕምሮ እንዲሄድ ያደርጋል፡፡
በዚህም አዕምሮ ይደብተዋል ይህንን ተከትሎ ወደ አልኮል መጠጦችም እንዲሄዱ እንደሚገፋፋ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡

5.ጥሩ የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋል
በአፍ ውስጥ በርካታ ባክቴሪያዎች ይገኛሉ እነዚህ ባክቴሪያዎች ደግሞ ስኳሩን ስለሚመገቡ ጥርስ ላይ አደጋ ያደርሳሉ እንዲሁም መልካም የሚባል የአፍ ጠረን እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡

6.እንቅልፍ አልባ ሌሊቶች እንዲከሰቱ ያደርጋል

አብዛኛውን ጊዜ ከምግብ በኃላ የምንመገባቸው ጣፋጭ ኬኮች ለእንደዚህ ዓይነት እክል እንደሚዳርጉ ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
ሆኖም ከፍተኛ የሆነ የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦችንና መጠጦችን ስንወስድ እንቅልፍ አልባ የሆኑ ለሊቶችን ለማሳለፍ እንደምንገደድ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡

7.የሰውነት የመከላከል አቅምን ያዳክማል

ከፍተኛ የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦችንና መጠጦችን መውሰድ የሰውነት የመከላከል አቅምን አዳክሞ ቀላል በሚባሉት ጉንፋንና ኢንፌክሽን የመጠቃት እድልን ያሰፋል ባስ ሲልም ለካንሰር ይዳርጋል፡፡

8.አዕምሮ ላይ እክል ያስከትላል
ስኳር በአዕምሮ ውስጥ ያለውን ፕሮቲን እንዲቀንስ ያደርጋል በዚህም ቀላል የሚባሉ የማስታወስ እክሎችን እንዲፈጠሩ ያደርጋል፡፡

9.የቆዳ መሸብሸብን ያስከትላል
ስኳር የሰውነት ቆዳ ለስላሳና ጤናማነቱን ጠብቆ እንዲሄድ የሚስችለው ሆርሞን ላይ እክል ይፈጥራል፡፡
ታዲያ ከላይ የተጠቀሱ በከፍተኛ የስኳር አወሳሰድ ምክንያት የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመከላከል መጠኑን መቀነስ እንደሚገባ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡
በዚህ ምክንያት ተፈጠረ የሚሉት ችግር ካስተዋሉ ወደ ህክምና ተቋም ሄደው ሐኪም ማማከሮን አይርሱ፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.