ያልተፈለገ የሰውነት ውፍረት የሚያመጣው የሰውነት ውስጥ ንጥረ ቅመም/ኢንዛይም/ እንዳገኙ ተመራማሪዎች ገለጹ።
የኮፐንሄገን ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች የአዲሱን ጥናት ውጤት በአይጦች ላይ ባደረጉትጥናት እና ምርምር እንዳረጋገጡም ነው የተገለጸው።
በጥናቱም በሰውነት ውሰጥ የሚገኝ ኤን ኤ ኤም ፒቲ የተባለ ንጥረ ቅመም /ኢንዛይም/ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት እንደሚዳርግ ነው የተመለከተው።
በዚህም ተመራመሪዎች አይጦችን በ2 ቡድን በመክፈል የአንደኛውን ቡድን ንጥረ ቅመሙ ከሰውነታቸው እንዲወገድ በማድረግ በስብ የበለጸገ፣ መካከለኛ ስብ ያለውና በስብ ይዘቱ ዝቅተኛ የሆነ ምግብ በተለያየ ጊዜ እንዲመገቡ ማድረጉን ነው የተገለጸው።
ሁለቱም ቡድኖች የስብ ይዘቱ ዝቅተኛ የሆነ ምግብ ሲመገቡ የሰውነት ክብደት ልዩነት ያላሳዩ ሲሆን፥ በስብ የበለጸገ ምግብ በተመገቡበት ጊዜ ግን ንጥረ ቅመሙ ከሰውነታቸው ያልተወገደው ቡድን አባላት ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት ተጋልጠው ታይተዋል ተብሏል።
ንጥረ ቅመሙ ከሰውነታቸው የተወገደላቸው አይጦች በተከታታይ በርገርና ፒዛ የተመገቡ ቢሆንም እንኳ ላልተፈለገ የሰውነት ክብደት እንዳልተጋለጡና በደማቸው ውስጥም ያለው የስኳር መጠንም ከሌሎቹ ተጠኝዎች አንፃር ለጤና ተስማሚ እንደሆነ ነው በጥናቱ የተገለጸው።
የጥናቱ ጸሃፊ እና በኖቮ ኖርዲስክ ፋውንዴሽን የመሰረታዊ የሰውነት ውስጥ ንጥረ ቅመሞች ውህደት ተመራማሪ የሆኑት ካረን ኖርጋርድ ኔልሰን አዲሱ ግኝት በተማሳሳይ ችግሩ ያለባቸው ሰዎችን ለመርዳት እንዳሚያስችል ተናግረዋል።
በኖቮ ኖርዲስክ ፋውንዴሽ የሰውነት ውስጥ ንጥረ ቅመሞች ውህደት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ዛቻሪ ገርሃርት ግን ጉዳዩ አሳሳቢ ቢሆንም ንጥረ ቅመሙ ከሰውነት ውስጥ እንዲወገድ ማድረጉ ሰውነትን የሚጎዳና ለሌላ የጤና ችግር ሊዳርግ የሚችል መሆኑን መግለፃቸውን ነው ዘገባው የሚያስረዳው።
ግኝቱ በንጥረ ቅመሙ ላይ ለሚደረግ ተጨማሪ ጥናትና ምርምር የሚያነሳሳና ሌላ መፍትሄ ለማፈላለግ እድል የሚፈጥር መሆኑንም አስረድተዋል።
ንጥረ ቅመሙ በጨጓራ፣ በደምና በሌሎች የሰውነት ክፍሎች የሚገኝ ሲሆን፥ በሰውነት ውስጥ ምግብን ለማዋሃድ፣ ለጉበትና ጡንቻዎች ጤና አስፈላጊ ነው ተብሏል።
ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)
Medications who pull someone’s leg untreatable percussion expiratory pressure of their. sildenafil cost Hojffn jpxeph
credit score range free credit score free annual credit report official site get my credit score
check my credit score credit karma free annual credit report official site how to raise credit score fico credit score