ንፅህናው ባልተጠበቁ እንደ ባህር፣ ሀይቅ እና ኩሬ ያሉ ውሃዎች ውስጥ መዋኘት ለተለያ በሽታዎች በቀላሉ እንድንጋለጥ ያደርጋል አለ አዲስ የተሰራ ጥናት።
ንፅህና በሌለው ውሃ ውስጥ መዋኘት ለሆድ ቁርጠት፣ የጆሮ ሕመምና ሌሎች በሽታዎች በቀላሉ እንደሚያጋልጥም ተመራማሪዎች ገልፀዋል።
ተመራማሪዎቹ እንዳስታወቁት እንደ ባህር፣ ሀይቅ እና ኩሬ ያሉ ውሃዎች ውስጥ የሚዋኙ ሰዎች ለጆሮ ህመም በ77 በመቶ የመጋለጥ እድል ሲኖራቸው፤ ለጨጓራ ህመም ደግሞ በ29 በመቶ የተጋለጡ ናቸው።
በዚህ ጉዳይ ዙሪያ 19 ጥናቶች የተካሄዱ ሲሆን፥ በጥናቱ ላይም ከተለያዩ የአውሮፓና አሜሪካ ሀገራት የተወጣጡ 120 ሺህ ሰዎች ተሳትፈውበታል።
ባደጉ ሀገራት ያሉ ሰዎች በባህር በተደጋጋሚ መዋኘት ለአደጋ እንደማያጋልጣቸው ቢያምኑም፤ በጥናቱ የተገኘው ውጤትን በተደጋጋሚ ቢዋኙም ውሃው ንጹህ ካልሆነ ለበሽታዎች ተጋላጭ እንደሆኑ ያሳያል።
ጥናቱ ሰዎች በርካታ የጤና በርካታ ጠቀሜታ ካለው የውሃ ዋና በስጋት እንዲርቁ ሳይሆን፤ በጉዳዩ ዙሪያ ግንዛቤ ኖሯቸው እራሳቸውን መጠበቅ እንዲችሉ የተሰራ መሆኑንም ተመራማሪዎች ተናግረዋል።
ምንጭ ፦ ቢቢሲ