እርግዝና ወቅት ዝቅተኛ መጠን ያለው የሀይል ሰጪ ምግብ መውሰድ በሚወለደው ህፃን ልጅ ጤንነት ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚኖረው ተመራማሪዎች ገለፁ።
የሰሜን ካሮላይና ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ያደረጉት ጥናት እንደሚጠቀመው፥ በእርግዝና ወቅት የምትወስደውን ሀይል ሰጪ ምግብ የቀነሰች ወይም የተወች ነፍሰ ጡር ከወሰደችው የበለጠ የምትወልደው ልጅ ከነርቭ ጋር በተያያዘ ህመም የተጠቃ ልጅ የመውለድ እድሏ በ30 በመቶ ከፍ ያለ መሆኑን ጥናቱ ይጠቁማል።
የጥናት አድራጊዎቹ በእርግዝና ወቅት ዝቅተኛ መጠን ያለው ሀይል ሰጪ ምግብን የወሰዱ እናቶች የሚወለዱት ህፃናት ያሉባቸው የጤና እንከን ምናልባትም ለሞት ወይም ለአድሜ ልክ ህመም የሚዳርጋቸው ሊሆን እንደሚችል ነው ያስጠነቀቁት።
ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶች ከእርግዝና በፊት እና በእርግዝና ወቅት የነፍሰ ጡር እናቶች የምግብ አወሳሰድ በሚወለደው ህፃን ላይ ተፅእኖ እንዳለው ቢያሳዩም የአሁኑ ለየት የሚያደርገው የሀይል ሰጪ ምግብ አወሳሰድ ወሳኝ መሆኑን ማመላከቱ ነው ብለዋል።
በመሆኑም እናቶች ከእርግዝና በፊት እና በእርግዝና ወቅት በሀይል ሰጪ ምግብ እጥረት ሊመጣ የሚችልን በሽታ ለመከላከል ሀይል ሰጪ ምግቦችን ከመብላት ባለፈ የፎሊክ አሲድ ምንጭ የሆኑ በቫይታሚን ቢ 9 የበለፀጉ ምግቦችን ወይም መድሃኒት እንዲወስዱ መክረዋል።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)