በሽንት ናሙና አማካኝነት የሰውነታችንን ትክክለኛ ስነ- ህይወታዊ ዕድሜ ማወቅ ተቻለ

                    

ተመራማሪዎች በሽንት ናሙና አማካኝነት በቀላሉ ከትውልድ ቀናችን ጀምሮ ከሚሰላው የእድሜ ቁጥር ይልቅ ስነ-ህይወታዊ የሆነውን ዕድሜን ማወቅ መቻሉን ገለፁ።

በዚህ መንገድ ከእድሜ ጋር የተያያዙ በሽታዎችንና ሞትን የሚያስከትሉ ሁኔታዎችን መገመት እንደተቻለም አስታውቀዋል።

ጆርናል ፍሮንቲየር እንዳተተው ከሆነ የሰዎች ዕድሜ ሲጨምር በሽንት ውስጥ የሚገኘው ኦክሲዳቲቭ የሚባለው ንጠረ ነገር ጉዳት እየጨመረ እንደሚሄድ ገልጸዋል።

ከዚህ በመነሳትም በቀላሉ በሽንት ናሙና አማካኝነት መለካት መቻሉን ነው የተናገሩት።

ይህ አዲስ ጠቋሚ ሰውነታችን ምን ያህል ዕድሜ እንዳስቆጠረ ያሳያል፤ ዕድሜ ሲባል ግን ከትውልድ ጊዜ ጋር ተቆጥሮ የሚቀመጠውን ሳይሆን ከአካላችን ስነ-ህይወታዊ (ባዮሎጂካል) ዕድሜ አንፃር መሆኑን አስረድተዋል። 

 

በተመሳሳይ ዓመት የተወለደ ሰው ተመሳሳይ ዕድሜ ያለው ቢሆንም የሰውነት አካላችን በአንጻሩ የተለያየ የዕድሜ እርከን እንደሚያስመዘግብ ገልጸዋል።

አንዳዶች ያለበሽታ ረዥም ዕድሜ ሲኖሩ ሌሎች በበኩላቸቸው በአጭሩ ይቀጫሉ፤ ይህ የሚያመለክተው በዕድሜያችን ውስጥ የሚያጋጥሙ በሽታዎችን ተቋቁሞ የማለፍና ያለማለፍ ሁኔታ እንደሆነ ጠቅሰዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ስነ-ህየወታዊ የዕድሜ መለኪያ ከዕድሜ ጋር ግንኑነት ያላቸው በሽታዎችንና የህይወት ፍጻሜያችንን የመገመት አቅምም አለው ነው ያሉት።

ይህ አዲሱ ግኝት ምናልባትም ከትውልድ ቀናችን ጀምሮ ከምንቆጥረው ዕድሜ በተሻለ ሁኔታ የሰውነታችንን ትክክለኛ አቋም ሊገልጽ እንደሚችል አጥኚዎቹ ጠቁመዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement