ሰላጣ፣ ቆስጣና ጥቅል ጎመን አዘውትሮ መመገብ የአእምሮን ቶሎ የማርጀት እድል በ10 ዓመት ይቀንሳል – Daily Serving Of Kale, Spinach Or Lettuce Could Slow Brain Ageing By Decade

                                                        

በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ አረንጓዴ ቅጠል ያላቸው ተክሎችን አዘውትሮ መመገብ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት ከዚህ ቀደም የተሰሩ በርካታ ጥናቶች አመላክተዋል።

ከሰሞኑ የወጣ አዲስ ጥናት ደግሞ እንደ ሰላጣ፣ ቆስጣ እና ጥቅል ጎመን ያሉ አረንጓዴ ቅጠል ተክሎችን በእለት ተእለት ምግባችን ውስጥ አካቶ መመገብ አእምሯችን ሎቶ እንዳያረጅ ያደርጋል ብሏል።

በእለት ምግባቸው ውስጥ ቢያንስ አንግ ዲዜ የሚገቡ ሰዎች ከማይመገቡት ጋር ሲነፃፀሩም፤ አብዝተው የሚመገቡ ሰዎች አእምሮ የበለጠ ወጣት ሆኖ ተገኝቷል።

በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው የአእምሮ እድሜ ልዩነት በአንድ ታላቅ እና ተናሽ ወንድም መካከል ያለ የ11 ዓመት እድሜ ልዩነት ያክል መሆኑነም ጥናቱ ጠቁሟል።

ጥናቱ በ960 ሰዎች ላይ የተካሄደ ሲሆን፥ የጥናቱ ተሳታፊዎች እድሜ በአማካኝ 81 ዓመት የሆኑ እና ከአእምሮ ጋር የተያያዘ ቸግር የሌለባቸው ናቸው።

በጥናቱ ተሳታፊዎች ላይም ለ5 ዓመታት ከተትል መደረጉን ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት።

ተመራማሪዎቹ የጥናቱ ተሳታፊዎችን እንደ አትክልት ተመጋቢነታቸው በአምስት ቡድን ከፋፍለው ነው ጥናቱን ያካሄዱባቸው።

በዚህም እንደ ሰላጣ፣ ቆስጣ እና ጥቅል ጎመን ያሉ አረንጓዴ ቅጠል ተክሎችን አዘውትረው የሚመገቡ ሰዎች አእምሮ በጣም ዝቅተኛ ከሚመገቡት ጋር ተነፃፀረው ታይተዋል።

በተገኘው ውጤተም አረንጓዴ ቅጠል ተክሎችን አዘውትረው የሚመገቡ አእምሮ ቶሎ የማርጀት እድሉ ዝቅተኛ ሆኖ መታየቱን ተመራማሪዎቹ ገልፀዋል።

በእለት ምግባችን ወስጥ እንደ ሰላጣ፣ ቆስጣ እና ጥቅል ጎመን ያሉ አረንጓዴ ቅጠል ተክሎችን ብቻ ቀላቅሎ በመመገብ አእምሯችንን ጤንነት በቀላሉ መጠበቅ እንችላለን ሲሉም ተመራማሪዎቹ አስታውቀዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement