የመገጣጠሚያ ሕመም – Joint Pain

                                                                         

መገጣጠሚያዎ ላይ ሕመም ይሰማዎታል? ምን እንደሆነስ ያውቃሉ?

ይህ የመገጣጠሚያ ሕመም በአገራችን የብዙ ሰዎች ችግር እየሆነ መጥቷል፡፡
የመገጣጠሚያ ሕመም በሕክምናው ቋንቋ አርተራይተስ (Arthritis) የምንለው ሲሆን የሚከሰትባቸው ምክንያቶች ደግሞ የተለያዩ ናቸው፡፡

የተለመደው የሕመም ዓይነት በዕድሜ ወይንም በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰተው የመገጣጠሚያ ሕመም ሲሆን ሌሎች የመገጣጠሚያ ሕመም ዓይነቶችም በሰውነታችን በሚከሰቱ አለርጂ (Autoimmune Related) ምክንያት ያመጣሉ፡፡
እነዚህም፡- 
• ሮማተቶይድ አርተራይተስ (Rheumatoid Arthritis )
• ሶሪያቲክ አርተራይተስ (Psoritic arthritis) በመባል ይታወቃሉ፡፡

የመገጣጠሚያ ሕመም ያላቸው ሰዎች በተጠቃው መገጣጠሚያ ላይ ከፍተኛ የሕመም ስሜት ይሰማቸዋል፡፡ ይህም የሚሆነው በመገጣጠሚያው አካባቢ ባሉ ጡንቻዎች መቆጣት ምክንያት ነው፡፡

የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
በኢንፌክሽን ምክንያት የሚከሰትን የመገጣጠሚያ ሕመም ምልክቶች
• ትኩሳት
• ብርድ ብርድ ማለት
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም (ውጋት)

በአለርጂ ምክንያት የሚከሰት የመገጣጠሚያ ሕመም
• የመገጣጠሚያ ላይ ሕመም ከእብጠት ጋር
• በጣት፤በእጅ እና በእግር መገጣጠሚያዎች ላይ
• ሕመሙ በድንገት የሚከሰትና ምክንያቱ ያልታወቀ ከሆነ
• ሕመሙ ከትኩሳት ጋር የተያያዘ ከሆነ
• ከፍተኛ ሕመምና መገጣጠሚያ አካባቢ ላይ መውላት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና 
ማዕከል መሄድ አስፈላጊ ነው፡፡

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement