የጆሮ ኢንፌክሽን – Ear Infection

                                                   

በደንበኞቻችን ጥያቄ መሰረት ለዛሬ የጆሮ ኢንፌክሽንና ምልክቶቹን በተመለከተ ባለሙያዎቹ የጻፏቸውን ጽሁፎችና ሙያዊ አስተያየቶቻቸውን ከዚህ በታች እንመልከት። 

የጆሮ ኢንፌክሽን በባክቴሪያ ወይንም በቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ችግር ሲሆን ከ3 ወር እስከ 3 ዓመት ባሉ ሕፃናት ላይም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህመሙ ሊጠቁ ይችላሉ፡፡የጆሮ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ የላይኛውን የአየር ቧንቧ ከሚያጠቁ በሽታዎች ጋር ተያይዞ የሚመጣ በሽታ ነው፡፡የላይኛውን የአየር ቧንቧ የሚያጠቁ በሽታዎች በሚኖሩ ጊዜ የጆሮን የመካከለኛውን ክፍል እና ጉሮሮን የሚያገናኘው ቱቦ (eustachian tube) ያብጥና አየር ወደመካከለኛው የጆሮ ክፍል እንዳይገባ ያደርጋል፡፡ ይኼም በመካከለኛው የጆሮ ክፍል ውስጥ ፈሳሽ እንዲጠራቀም እና ለባክቴሪያ አመቺ የመራቢያ ሁኔታን እንዲፈጥር ያደርጋል፡፡ ባክቴሪያ ከተራባ በኋላ
በአካባቢው ያሉ ህዋሶችን በመግደል መግል እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡
የጆሮ የኢንፌክሽን ምልክቶች
• የጆሮ ሕመም
• የጆሮ መደፈን ስሜት
• የራስ ምታት
• ከጆሮ የሚወጣ ፈሳሽ
• ጆሮ ውስጥ የሚጮህ ስሜት
• የመስማት ብቃት መቀነስ እና ማቆም
• አዲስ የተወለዱ ሕፃናት ደግሞ በእጃቸው ወደ ጆሮ አካባቢ በተደጋጋሚ ይነካካሉ
• መቅለሽለሽ እና ማስመለስ
• ማስቀመጥ
• ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት መጠን መጨመር

ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement