ሄፓታይትስ “ሲ”(Hepatitis C) ምንም ምልክት ሳያሳይ በደም ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመቀመጥ እየተራባ ሄዶ ስር የሰደደ የጉበት መቆጣት መንስኤ ሊሆን ይችላል።
ሄፓታይተስ የሚከሰተው ደግሞ ሄፓታይተስ ኤ፣ ቤ፣ ሲ፣ ዲ እና ኢ ተብለው በሚጠሩ አምስት ዋና ዋና ቫይረሶች መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።
የሄፓታይተስ ሲ ቫይረስ ለብዙ ዓመታት በሰውነት ውስጥ ተደብቆ በመቆየት ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ የጉበት በሽታ እና ካንሰር ሊያመጣ የሚችል በሽታ በመሆኑ ድምፅ አልባው ገዳይ ብለው ባለሙያዎች ይጠሩታል።
ብዙ ሰዎች የሄፓታይትስ ሲ ምልክቶች ስለማያዩ ወይም ምን ያህል የተጎዱ እንደሆኑ ስለማያውቁ ለብዙ ዓመታት የህክምና ምርመራ አያደርጉም ነው የተባለው።
በዚህም የበሽታው ምልክቶች በራሳቸው ጊዜ መታየት ሲጀምሩ ወይም ምርመራ ሲደረግ ብዙውን ጊዜ ጉዳቱ የከፋ እንደሚሆን ተነግሯል።
በጣም የተለመዱ የሄፖታይትስ ሲ ምልክቶች ከሚከተሉት መካከል የሚከተሉት ይገኛሉ።
ድካም
ትኩሳት
የጡንቻ ወይም የመገጣጠሚያ ህመም
የምግብ ፍላጎት መቀነስ
የማቅለሽለሽ
በሆድ የላይኛው የቀኝ ክፍል ላይ የሚከሰት ህመም
ደማቅ ቢጫ መልክ የያዘ ሽንት
ማስመለስ
ብጫ ቆዳ ወይም ዓይኖች
የቆዳ ማሳከክ
የሰገራ መንጣት
የደም መፍሰስ
ቀጭን ሰንበር
የሄፓታይትስ ሲ ህክምናዎች
የሄፕታይትስ ሲ የመከላከያ ህክምና ባለፉት ዓመታት በከፍተኛ ሁኔታ መሻሻሉ ተገልጿል።
እየተሻሻሉ የመጡት መድሃኒቶቹም ቫይረሱን ለማስቆም የበለጠ ውጤታማ ናቸው ነው የተባለው።
በመሆኑም በበሽታው ላይ በቂ ግንዛቤ ጨብጦ የተጠቂ ሰዎችን ችግር ለመቀነስ እና በሽታውን ለመከላከል የተሟላ የጉበት ምርመራዎችን ጨምሮ መደበኛ ምርመራዎችን ማካሄድ ይመከራል።
ለዚህም የሄፓታይትስ ሲ ምልክቶች ተብለው የተጠቀሱትን ሲያስተውሉ ወዲያውኑ ለህክምና ባለሙያዎች ማማከር እንደሚገባ ተነግሯል።
ምንጭ:- ዶክተር አለ(Doctor Alle)