ምላሳችን ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?

                                              ምላሳችን እንደ አንድ የሰውነታችን ክፍል ስለ ጤናችን በርካታ ጉዳዮችን ይናገራል።የምላሳችን ቀለም በመመልከት ብቻ ለተለያዩ ችግሮች መጋለጣችንን መረዳት እንችላለን።ይሁን እንጂ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት የምላስ ቀለም ለውጦች ሲያጋጥሙን ወዲያውኑ ወደ ህክምና ተቋማት በማምራት ሀኪሞችን ማማከር ተገቢ ነው።
1. ቀላ ያለ ምላስ
– ምላሳችን ይህን አይነት ቀለም ሲኖረው ሰውነታችን እንደ ቫይታሚን ቢ 
ኮምፕሌክስ እና አይረን ያሉ ንጥረ ነገሮች እጥረት እንዳጋጠመው የሚያሳይ
ነው።
– አንዳንድ የባህላዊ መድሃኒት አዋቂዎች ደግሞ ይህ ሁኔታ በአንድ በተወሰነ
የሰውነታችን ክፍል ሙቀት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ይላሉ።
– የጥርስ ሳሙና፣ መድሃኒት አልያም አሲዳማ ምግቦች በአፍ ውስጥ
ከሚፈጥሩት ውህደት ጋር ተያይዞም ሊከሰት ይችላል።
2. ሀምራዊ ምላስ
– ለጉሮሮ ቁስል (ብሮንካይትስ) መጋለጥን የሚያሳይ ነው።
– ሰውነታችን በቂ ኦክስጂን አለማግኘቱንም ያመላክታል።
– ዝቅተኛ የደም ዝውውር እና ከፍተኛ የኮሊስትሮል መጠንንም ይጠቁማል።
– በጣም የቀዘቀዙ ምግቦችን እንዲሁም ነጭ ሽንኩርትና ዝንጅብል መውሰድ
ደግሞ ለችግሩ ሊያጋልጥ ይችላል።
3. ሻካራ እና ቢጫ ምላስ
– አነስተኛ የሆሞግሎቢን መጠንን ያሳያል።
– ድካም እና መዛል፣ ከሳንባ እና ትልቅ አንጀት ጋር የተያያዙ ችግሮችንም
ያመለክታል።
– ዝንጅብል፣ ቀረፋ እና ነጭ ሽንኩርት መጠቀም ከዚህ ችግር ለመውጣት
ይረዳል።
– የሄሞግሎቢን መጠንን ከፍ ለማድረግ እንደ ስፒናች፣ ቀይ ስር፣ አፕል፣ ቀይ ስጋ፣
ዘቢብ፣ ማንጎ፣ ለውዝ እና የመሳሰሉ የምግብ አይነቶችን መመገብ
ይመከራል።
4. ጥቁር ምላስ
– ከጊዜ ወደ ጊዜ የሰው ልጆች ምላስ ወደ ጥቁርነት እና ጸጉር የበዛበት መሆን
ይሸጋገራል።
– ጥቁርና ጸጉር የሚያወጣ ምላስ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል ነው
የሚነገረው።
– በምላስ ላይ የሚወጣው ጸጉር በአፍ ውስጥ ለባክቴሪያዎች መራባትና
ለቆሻሻዎች መጠራቀሚያነት በማገልገል በርካታ የጤና ችግሮችን ያስከትላል።
5. ነጭ ምላስ
– በምላስ ጸጉሮች ባክቴሪያዎች መሰግሰጋቸውን ያመለክታል።
– የሞቱ ህዋሳት እና ቆሻሻዎች በምላሳችን ጸጉሮች መመሸጋቸውንም
ያመለክታል።
– ሲጋራ ማጨስ፣ የውሃ ጥም፣ የአፍ መድረቅ እና መሰል ምክንያቶች ለችግሩ
በምክንያትነት ይጠቀሳሉ።
6. ቀይ ምላስ
– በአብዛኛው በህጻናት ጤና ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን ያሳያል።
– የእንጆሪ ቀለም ያለው ምላስ ደግሞ ህጻናት ለትኩሳት እና የደም ስሮችን
ለሚያጠቃ በሽታ መጋለጣቸውን ያመለክታል።
– ይህ አይነት ቀለም ያለው ምላስ በወጣቶች ላይ ብዙ ጊዜ አይታይም።
– ምላሳችን በጣም ለስላሳና ቀይ ከሆነ የቫይታሚን ቢ በተለይም የኒያሲን
እጥረት እንዳጋጠመን ያሳያል።
7. ግራጫ ምላስ
ይህ ደግሞ ሜላኖማ ለተባለ የቆዳ ካንሰር በሽታ መጋለጥን ያሳያል።
8. ቀይ ነጠብጣቦች የበዙበት ምላስ
– በምላስ ላይ የሚታዩ ቀይ ነጠብጣቦች የበርካታ ችግሮች ምልክት መሆናቸው ይነገራል።
– ከቫይታሚን ሲ የሚገኙ ባዮፍላቮዶይሶችን በበቂ ሁኔታ አለማግኘትን ያመለክታል።
– ትኩስ መጠጦችን ማዘውተር ለችግሩ በምክንያትነት ይጠቀሳል።
– የአስም እና የተለያዩ አለርጂዎች ምልክትም ነው።
9. ደረቅ ምላስ
– ሰውነታችን በርካታ ንፍጥ እያመረተ መሆኑን ያሳያል።
– ችግሩን ለመፍታት ከስኳር ምርቶችና ከወተት ተዋጽኦዎች መራቅ ያስፈልጋል።
– ጭንቀት ምራቅ አመንጪ እጢዎች እንዲያብጡ በማድረግ ምላስ እንዲደርቅ የማድረግ አቅም አለው።
– አንድ ብርጭቆ የሎሚ ውሃ መጠጣት የምላስ ድርቀትን ለማስወገድ ይረዳል።
10. ያበጠ ምላስ
– ለአለርጂ ወይም ኢንፌክሽን የመጋለጥ እድልን ያመለክታል።
– የቫይታሚን ቢ 12 እጥረትንም ያሳያል።

ምንጭ:- ዶክተር አለ

ምላሳችን ስለ ጤናችን ምን ይናገራል?

Advertisement