በዩናይትድ ስቴትስ ከ37 ሴቶች መካከል አንዷ በጡት ካንሰር በሽታ ህይወቷ እንደሚያልፍ ጥናቶች ያሳያሉ።
የአሜሪካ የካንሰር ማህበር እንደሚለው 2017 ብቻ በአገሪቱ 40 ሺህ ሴቶች በካንሰር ህመም ህይወታቸው ያልፋል።
ባለሙያዎች እንደሚሉት፥ ብዙ ሴቶች ምንም ዓይነት የበሽታው ምልክት ሳይታይባቸው የጡት ካንሰር ህክምናን የሚከታተሉ ሴቶች ብዙ ናቸው።
ይሁን እንጂ የማያቋርጥ ሕመም እና መድረቅን የመሰሉ የተወሰኑ የህመም ምልክቶች ይታያሉ።
ባለሙያዎች ሴቶች ሁል ጊዜ መደበኛ የሆነውን የጡታቸውን ጤንነት ካልተለመደው በመለየት ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ይመክራሉ።
ያልተለመዱ የጡት ጤንነት ገፅታዎች የሆኑ የካንሰር ህመም ምልክቶች ናቸው ያሏቸውንም ይዘረዝራሉ፦
የጡት ቆዳ ያልተለመደ ቀለም ሲይዝ፣
እንግዳ በሆነ መልኩ ከጡት ጫፍ ፈሳሽ ወይም ደም ሲወጣ ወደ ህክምና መሄድ አስፈላጊ መሆኑንም ተጠቁሟል። ይሁን እንጂ ከጡት ጫፎች የሚወጣው ደም አስቀድሞ የካንሰርን ምልክት ነው ብሎ መደምደም አይቻልም ነው የተባለው።
የቆዳ መቅላት እና የጡት ማተኮስ የካንሰር ምልክቶች ናቸው ተብሏል።
በጡት ላይ የሚታይ ህመምም ቀላል የካንሰር ምልክት መሆኑን የካንሰር ህክምና ባለሙያዎቹ ጠቁሞዋል።
ባለሙያዎች ታካሚዎች እንደነዚህ ዓይነት ምልክቶች ሲታዩባቸው አስቀድመው ካልታከሙ የአጥንት ህመም እና ካንሰሩ አስቀድሞ ከተሰራጨም የአጥንት መሳሳት ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ያስጠነቅቃሉ።
ስለዚህ በጡት አከባቢ ከላይ የተዘረዘሩት ዓይነት ምልክቶች ሲታዩ ተሎ ወደ ህክምና በመሄድ ባለ ሙያን ማማከር እና አስፈላጊውን ምርመራ ማካሄድ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)