ማግኒዚየም በሰውነታችን ውስጥ ከመጠን በላይ ሲበዛ ወይም ሲያንስ የአዕምሮ ህመም ያስከትላል

“>ውሮሎጂ በተባለው መጽሔት ላይ የወጣው አዲስ ጥናት እንደሚያሳየው፥ በጣም ከፍተኛ ውይም ዝቅተኛ የማግኒዚየም መጠን የአዕምሮ ህመም በማስከተል የሰዎችን በመርሳት በሽታ የመያዝ እድላቸውን ከፍ ሊያደርገው ይችላል።

የስንዴ ዱቄት፣ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ሙዝ እና የመሳሰሉት ከማግኒዚየም ምንጮች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ዝቅተኛ የማግንዚየም መጠን የሚባለው በአንድ ሊትር እስከ 0 ነጥብ 79 ሚሊ ሊትር የሚደርስ ሲሆን፥ ከፍተኛ የማግኒዚየም መጠንም በአንድ ሊትር እስከ 0 ነጥብ 90 ሚሊ ሊትር ሊደርስ እንደሚችል ተገልጿል።

ጥናቱ የተካሄደው በ9 ሺህ 569 ሰዎች መሆኑን ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

ለጥናት በናሙና የተሳተፉት ሰዎች ከመጀመርያው የአእምሮ ችግር አልነበራቸውም ተብሏል።

ለስምንት ዓመታት ያህልም ክትትል የተደረገላቸው መሆኑም ጭምር በጥናቱ ቀርቧል።

በክትትል ወቅቱ ለናሙና ከቀረቡት 823 ሰዎች በአእምሮ ሕመም መያዛቸው፥ ከእነዚህ ውስጥ 662 ሰዎች የአልዛይመር በሽታ እንዳለባቸው መረጋገጡ ተገልጿል።

በተጨማሪም የማግኒዚየም ደረጃዎቻቸው ከፍተኛ እና ዝቅተኛ የሆኑት ቡድን በአማካይ ከነበሩት ጋር ሲነጻጸር በአእምሮ በሽታ የመያዝ ዕድላቸው ከፍተኛ ሲሆን፥ 30 በመቶ ደግሞ በተለየ መልኩ የመዘንጋት ችግር አጋጥሟቸዋል ተብሏል።

የማግኒዚየም ደረጃዎችም በአምስት የተከፈሉ ሲሆን፥ ተመራማሪዎቹ በአዕምሮ ችግር እና በማግኒዚየም ማነስ ወይም መብዛት መሃከል ጋር ያለውን ግንኙነት በመመርመር ሶስተኛው ደረጃ ማጣቀሻ ተጠቅመዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement