በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት በየአመቱ የሚደረገው የ12ኛው የአዲስ አበባ ሲቲ ካፕ ውድድር በ2010 በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚደረግ ሲሆን ፌዴሬሽኑም የውድድሩን ጅማሮ ቀን መስከረም 27 እንዲሁም የውድድሩነ የፍጻሜ ቀን ደግሞ ጥቅምት 11 ማድረጉ ተነግሯል፡፡
እስካሁን በይፋ የሚሳተፉት ክለቦች ሙሉ በሙሉ ባልታወቁበት በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ ቡና ፣ ደደቢት ኢትዮ ኤሌክትሪክ በሲቲ ካፑ እንደሚሳተፉ ማረጋገጫ ሲሰጡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እስካሁን በዚህ ውድድር ላይ እሳተፋለው በማለት ለእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አላሳወቀም፡፡
ከዚህ ቀደም ከመስከረም 20 እስከ ጥር 4 ሊደርግ ታስቦ የነበረው ውድድር ከሰሞኑ በአዲስ አበባ እያጣለ ባለው ሀይለኛ ዝናብ ምክንያት አንድ ለእናቱ የሆነው አዲስ አበባ ስቴዲየም በዝናቡ ሜዳው እየጨቀየ የሚገኝ በመሆኑ እና ዝናቡም በዚህ የሚቀጥል ከሆነ ለመጫወት አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት ውድድሩን ለ ተጨማሪ አንድ ሳምንት ማስተላለፍ የግድ ብሏል፡፡
ባሳለፍነው አመት በተደረገው በዚህ ውድድር ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ቅዱስ ጊዮርጊስን በኢብራሂም ፎፋና ብቸኛ ግብ 1-0 በመርታት የውድድሩን ዋንጫ አሸናፊ መሆኑ የሚታወስ ነው፡፡
ምንጭ:- ኢትዮአዲስ ስፖርት