ቀይ ስር ለሰውነታችን የሚሰጣቸው የጤና በረከቶች

                                                              

ቀይ ስር በተለያዩ ንጥረ ነገሮች የበለፀገ ለምግብነት የሚውል አትክልት ነው።

ይህ አትክልት በስራ ወይም በአካላዊ እንቅስቃሴ የደከሙ ጡንቻዎቻችንን ለማበርታት እንደሚያስችል የኖርዝአምብሪያ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ገልፀዋል።

ቀይ ስር ለአንጎልና ለሌሎች የሰውነት ክፍሎችም በርካታ ፋይዳዎች አሉት።

የደም ግፊትን ለመቀነስና ዝውውሩን ለማፋጠን ይጠቅማል።

ይህ የአትክልት ዘር በሮማውያን ዘመን በጣም ተወዳጅ ምግብ የነበረ ሲሆን፥ ለቁስል፣ ለቆዳ ህመም፣ ለትኩሳትና መሰል ህመሞች መድሃኒትነት ይጠቀሙበት ነበር።

ቀይ ስር በስራስር የአትክልት ምግብ የሚመደብ ሲሆን በውስጡም የተለያዩ ንጥረነገሮችን የያዘ ነው።

በፖታሺየም፣ ማግኒዥየም፣ አይረን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቢ6 እና ሲ፣ ፎሊክ አሲድ፣ ካርቦሃይድሬት፣ ፕሮቲን፣ እና በሌሎች ንጥረነገሮች የበለፀገ መሆኑን ጥናቶች ያሳያሉ።

በናይትሬት የበለፀገ መሆኑም የደም ቧንቧዎች ተገቢውን ስራቸውን እንዲያቀላጥፍና የደም ግፍትን እንዲቀንስ በማድረግ ፋይዳው ላቅ ያለ ነው።

ደም ወደ አንጎል የሰውነታችን ክፍል በመደበኛ ሁኔታ እንዲደርስ በማገዝ የአእምሮ ስራዎች እንዲቀላጠፉ ያደርጋል።

የሰውነታችን ህዋሳት ስራቸውን በተገቢው ሁኔታ እንዲያከናውኑ የሚጠቅም ሲሆን፥ በተለይም ለነፍሰጡር ሴቶች በዚህ ረገድ የሚሰጠው ጥቅም ላቅ ያለ ነው።

ለልብ ጤንነት አስፈላጊ የሆነው ቀይ ስር በአይረን የበለፀገ መሆኑ፥ በቀይ የደም ህዋስ ውስጥ ኦክሲጅን በጥሩ ሁኔታ እንዲጓጓዝ ያግዛል ነው የተባለው።

የቫይታሚን ሲ ንጥረ ምግብ ይዘቱ ደግሞ ለሰውነታችን በሸታ የመከላከል አቅም ማደግና ለቆዳችን ጤናማነት መልካም መሆኑ ተነግሯል።

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement