ጭንቀት በጤናዎ ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ያውቃሉ?

                                             

1) የፀጉር መነቃቀል ያስከትላል አልፎም መመለጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡

2) በአንጎል ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ለእንቅልፍ እጦት፤ራስምታት፤መነጫነጭ፤መደበትና እና የባህርይ ለዉጥን ያስከትላል፡፡

3) በከንፈር ላይ የሚወጡ አንዳንድ ቁስለቶች ከጭንቀት ጋር የተያያዙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

4) ለደም ግፊት መጨመር በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭነትን ይጨምራል፡፡ ለልብ ሕመምም ይዳርጋል፡፡

5) በሳንባ ላይ የሚያስከትለው ችግር የአስም ሕመምተኞች ላይ የአዕምሮ ጭንቀት ሕመማቸው እንዲነሳባቸው ያደርጋል፡፡

6) በጡንቻዎች ላይ ሕመም ስሜት እንዲኖር ያደርጋል ለወገብ ሕመም ያጋላጣል፡፡

7) ጭንቀት የጨጓራ ሕመምን ከማስከተል ባለፈ ለአንጀት ቁስለትም ሊዳረግ ይችላል፡፡

8) ከፍተኛ የሆነ ጭንቀት የወር አበባ ዑደትን ያዛባል፡፡ ወንዶችን ለስንፈተ ወሲብ ስለሚዳርግ የትዳር እና የፍቅር ግንኙነት እንዲሻክር ያደርጋል፡፡

ስለዚህ ጭንቀትን በማስወገድ ጤንነትዎን ይጠብቁ፡፡

ምንጭ፦በዶክተር ሆነሊያት

Advertisement