የጉበት ስብ በሽታ ምንድን ነው ?መከላከያውስ?

                                         

የጉበት ስብ በሽታ ማለት አላስፈላጊ የሆነ ስብ በጉበት ላይ መከማቸት ማለት ነው።
የጉበት ስብ በሽታ መንስዔዎች
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
-በደም ውስጥ ያለ የስብ መጠን ከፍተኛ መሆን
-የስኳር ህመም
-በዘር ውስጥ የጉበት በሽታ ተጠቂ መኖር
-ለሌላ በሽታ የሚወሰዱ መድሀኒቶች

ለጉበት ስብ በሽታ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ መጠቀም
-ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ እና ከተገቢው በላይ መጠኑ ከፍ ያለ መድሀኒት መውሰድ ለምሳሌ:- ፓራሲታሞል
-እርግዝና
-ከፍተኛ የሆነ የኮሌስትሮል መጠን
-የተመጣጠነ ምግብ እጥረት መኖር
-ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አብዝቶ መመገብ

የጉበት ስብ በሽታ ምልክቶች
1.የምግብ ፍላጎት መቀነስ
2.የክብደት መቀነስ
3.የሆድ አካባቢ ህመም
4.የድካም ስሜት መኖር
5.ማዞር እና ከፍተኛ የሆነ የድካም ስሜት
6.ማቅለሽለሽ እና ወደ ላይ ማለት
7.በሆድ የላይኛው የቀኝ ክፍል ላይ ከፍተኛ ህመም መኖር

ጉበት በከፍተኛ ደረጃ ስትጎዳና ቁስለት ሲፈጠር …
1.በሆድ አካባቢ በፈሳሽ መሞላት እና እብጠት መኖር
2.የቆዳ እና የዓይን አካባቢ ወደ ቢጫነት መቀየር
3.በቀላሉ መድማት
4.ራስን መሳት
ውድ የዶክተር አለ ፔጅ ተከታታዮች የዚህ በሽታ መከላከያ መንገዶች እና ከተከሰተ በኋላ በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንደሚቻል በነገው እለት የምናቀርብ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን።

የጉበት ስብ በሽታን እንዴት መከላከል ይቻላል? 
-የአልኮል መጠጥ አብዝቶ አለመጠቀም
-ከሀኪም ትዕዛዝ ውጪ መድሀኒት አለመውሰድ
-የተመጣጠነ ምግብ መመገብ
-ቅባትነት ያላቸውን ምግቦች አለመመገብ

የጉበት ስብ በሽታ ከተከሰተ በኋላ በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል?
1.የፖም አቼቶን መጠቀም(Apple cider vinegar)
2.የሎሚ ጭማቂን በቀን ከ2-3 ጊዜ መጠጣት
3.በቀን ከ3-4 ሲኒ አረንጓዴ ሻይ መጠጣት
4.ግማሽ የሻይ ሲኒ እርድ ከግማሽ ብርጭቆ ለብ ያለ ውሃ ጋር በማዋሃድ በቀን 2 ጊዜ መጠጣት
5.መጨናነቅን ማቆም
6.ፓፓያን መመገብ
7.በቀን ከ8-10 ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት
8.በቂ እረፍት ማድረግ
9.አትክልትና ፍራፍሬን አዘውትሮ መመገብ
10.የሰውነት ክብደትን መቆጣጠር
11.በየጊዜው ወደ ጤና ተቋም በመሄድ ክትትል ማድረግ

 

ምንጭ:- ጤናችን

 

Advertisement