የደም ግፊት በሽታ መነሻዎች : ምልክቶች እና መከላከያ መንገዶች

                                                        

የደም ግፊት በሽታ የተለመደ ችግር ሲሆን የደማችን ጉልበት/ሀይል ከአርተሪ( የደም ቧንቧ) ግድግዳ ጋር ሲነፃፀር በጣም ከፍተኛ ሲሆን የሚከሰት ህመም ነው ይህም እንደ ልብ ህመም አይነት የጤና ችግር ያስከትላል። የደም ግፊት ልባችን በምትረጨው የደም መጠን እና ደም በአርተሪዎቻችን ውስጥ ሲያልፍ የመቋቋም ኃይል ይወሰናል።ብዙ ደም ልባችን በረጨች መጠን አርተሪያችን ይጠባል ከዚያም የደም ግፊታችን መጠናችን ይጨምራል ማለት ነው። ምንም አይነት ምልክት ሳይኖረው ለአመታት የደም ግፊት መጠናችን ከፍተኛ ሊሆን ይችላል ይህም የደም ቧንቧዎቻችንን ይጐዳቸዋል። ያልተቆጣጠርነው ከፍተኛ የደም ግፊት ለከባድ የጤና ችግር የመጋለጥ እድላችንን ይጨምራል ለዚህም የልብ ድካምና የደም መርጋት ተጠቃሾች ናቸው።የደም ግፊት ከብዙ አመታቶች በፊት የነበረ በሽታ ሲሆን በማንኛውም የእድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ያጠቃል። ከፍተኛ የደም ግፊት በቀላሉ የሚታወቅ በሽታ ሲሆን በሽታው እንዳለብን ካወቅን ሀኪም በማማከር በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል።

የደም ግፊት በሽታ መነሻዎች
ሁለት አይነት የደም ግፊት በሽታዎች አሉ
1. የመጀመሪያ የደም ግፊት አብዛኞቻችን አዋቂዎች የደም ግፊት መነሻ ምክንያት አይታወቅም። የዚህ አይነቱ የደም ግፊት የመጀመሪያ ደረጃ ይባላል የሚከሰተውም ቀስ በቀስ ከረጂም አመታት ቆይታ በኃላ ነው።
2. ሁለተኛ የደም ግፊት አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ የደም ግፊት ከተች በተጠቀሱት ምክንያቶች ያጋጥማቸዋል። ይህ አይነቱ የደም ግፊት ሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ይባላል በድንገት የሚከሰት ሲሆን ከመጀመሪያ ደረጃ የደም ግፊት ዓይነት የበለጠ ከፍተኛ የደም ግፊት በሽታ ያስከትላል። የተለያዮ ሁኔታዎችና መድሃኒቶች ለሁለተኛ ደረጃ የደም ግፊት ያጋልጡናል እነሱም:-
* የኩላሊት ችግር
* የአድሬናል ዕጢ እብጠት
* የታይሮይድ ችግር
* ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ችግር
* አንዳንድ መድሃኒቶች
* በህግ የተከለከሉ መድሃኒቶች (ኮኬይን፣ አምፊታሚን)
* የአልኮል ሱሰኝነት
* የእንቅልፍ ችግር

የደም ግፊት ምልክቶች
አብዛኛው የደም ግፊት በሽታ ተጠቂ ሰዎች የደም ግፊት መጠናቸው በአስደንጋጭ ሁኔታ እስከሚጨምር ድረስ ምንም አይነት የበሽታው ምልክት አይታይባቸውም።ጥቂት ሰዎች በመጀመሪያ የበሽታው ደረጃ ላይ የሚገኝ ከባድ የራስ ምታት፣ የተምታታ ንግግር እና ከሌላጊዜ የበለጠ የአፍንጫ መድማት ያጋጥማቸዋል። እነዚህ ምልክቶች የደም ግፊት መጠናቸው ለህይወታቸው አስጊ እስከሚሆን ድረስ አይታዮም።የደም ግፊት መጠንዎን መለካት እንደማንኛውም የሀኪም ቀጠሮ ልንወስደው ይገባል። ከ18 ዓመት ጀምሮ ቢያንስ በ2 ዓመት አንድ ጊዜ እንድንለካ ይመከራል። የደም ግፊትዎን ሲለኩ በሁለቱም ክንድዎ መለካትአለብዎት የደም ግፊት በሽታ ካለብዎት ወይም የልብ ችግር ካለብዎት በተደጋጋሚ መለካት ተገቢ ነው። በተወሰነ የጊዜ ልዮነት የጤና ምርመራ የማያደርጉ ከሆነ በፋርማሲና በተለያዮ ቦታዎች በሚገኙ የደም ግፊት መለኪያ መሳሪያዎች እንዲለኩ ይመከራል።

የደም ግፊት መከላከያ መንገዶች
ጤናማ የሰውነት ክብደት ከመጠን ያለፈ ውፍረት ከ2―6 እጥፍ በደም ግፊት የመያዝ እድላችንን ይጨምራል።በየጊዜው እንቅስቃሴ መስራት የሰውነት እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰዎች ከ 20-50% ከማያደርጉት ሰዎች የመያዝ ዕደላቸውን ይቀንሳል። እንቅስቃሴ ሲባል ማራቶን መሮጥ አይጠበቅብንም በየቀኑ የሚደረግ ትንሽ እንቅስቃሴ በቂ ነው።የጨው አጠቃቀማችንን መቀነስየደም ብዛት ያለባቸው ሰዎች ጨው መጠቀማቸውን ሲያቆሙ የደም ግፊት መጠናቸው ይቀንሳል። ጨው መጠቀም ም ማቆም የደም ግፊት መጠናችን እንደይጨምር ያደርጋል። አልኮል መጠጦችን መጠጣት ብዛት ያለው አልኮል መጠጣት የደም ግፊታችን እንዲጨምር ያደርጋል። የደም ግፊታችንን ለመቀነስ የሚወስድትን የአልኮል መጠን ገደብ ማስቀመጥ ተገቢ ነው።ጭንቀትን መቀነስ ጨንቀት የደም ግፊት መጠናችንን እንዲጨምር ያደርገዋል ከጊዜ ቆይታ በኃላ ለደም ግፊት በሽታ መነሻ አንድ ምክንያት ይሆናል። ሌሎች የምግብ ይዘቶች የደም ግፊት በሽታን ለመከላከል ይረድናል ከነዚህም መካከል ፖታሲየም― በፖታሲየም የበለፀጉ ምግቦች በደም ግፊት በሽታ ከመያዝ ይከላከላሉ። ፖታሲየም ከተለያዮ አትክልትና ፍራፍሬዎች፣ ከእንሰሳት ተዋጽኦዎች እና ከአሳ እናገኛለን።ካልሲየም፦ አነስተኛ የካልሲየም መጠን የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች በደም ግፊት የመያዝ ዕድላቸው ይጨምራል። ካልሲየም ከወተት፣ እርጐና አይብ እናገኝዋለን።ማግኒዚየም፦ የማግኒዚየም መጠናቸው አነስተኛ የሆኑ ምግቦች መመገብ የደም ግፊት መጠናችንን ይጨምራል። የጤና ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ተጨማሪ ማግኒዚየም የደም ግፊትን ለመከላከል መውሰድ አይመከርም ከመደበኛ ምግባችን የምናገኝው በቂ ስለሆነ።የአሳ ዘይት፦ ኦሜጋ 3 ፋቲ አሲድ የምናገኝው ከአሳ ሲሆን የደም ግፊትን በመከላከል ይረዳናል።ነጭ ሽንኩርት፦ የደም ግፊት መጠንን እና ኮሌስትሮልን በማስተካከል ከፍተኛ ጥቅም አለው። የካንሰር በሽታን ይከላከላል።

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement