እርድ የጣፊያ ካንሰርን ለመከላከል ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንድ ጥናት አመላከተ

                                           

 በአሁኑ ወቅት የጣፊያ ካንሰር ህክምና በበሽታ እና በመድሃኒት መላመድ ምክንያት ፈታኝ መሆኑን ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡

የአሜሪካ ተመራማሪዎች የምርምር ውጤት ይህን የካንሰር ዓይነት የሚያክም የመድሃኒት ስሪት ለመቀመም እርድ ዋነኛ ግብዓት መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

አዲሱ በዋናነት ከእርድ እና ሌሎች ውስን ቅመሞች የተሰራው ከርኩዩሚን መድሃኒት ካንሰር፣ ስኳር እና ሌሎች በሽታዎችን ለማከም የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

ሆኖም በእንክብል መልክ የተዘጋጁት መድሃኒቶች በአፍ በሚዋጡበት ጊዜ በፍጥነት ተዋህደው ከሰውነት አካላችን በመጥፋት በሽታውን የማጥፋት አቅማቸው ደካማ እንደሆነ ተነግሯል።

ለዚህ ችግርም በቀጣይ ከፍተኛ የህክምና ሙከራዎችን በማድረግ የቅመማ ሂደቱ ላይ የተፈጠረ ችግር ነው ወይስ ሌሎች አብረው የተቀየጡ ግብዓቶች ያመጡት ጫና የሚለው እንደሚጠና ተነግሯል፡፡

ለዚህም ተመራማሪዎች በባህላዊ መንገድ እርድን በመጠቀም የጣፊያ ካንሰርን ለማከም ከሚደረገው ሂደት ተሞክሮ ለመውሰድ አስበዋል፡፡

በተለይም ተፈጥሯዊውን እርድ እንደ ምግብ ተጠቅመው ከህመሙ የሚድኑበትን መፍትሔ ለማምጣት ጥረት እንደሚደረግ ነው የተናገሩት፡፡

ጥናቱ በዳላስ የባይለር ሰኮት እና ኋይት የምርምር ኢንስቲትዩት እንዲሁም በሌሎች ተመራማሪዎች የተሰራ ነው።

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement