ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው መድሀኒቶች ትኩረት የሚሹ በሽታዎችን ለመከላከል ተሰራጭተዋል::

                                        

በሰለሞን ጥበበስላሴ

ከ4 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን አራት ዓይነት መድሀኒቶች ትኩረት ይሻሉ ተብለው የተለዩ ስምንት ዓይነት በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ እንዲውሉ አሰራጭቻለሁ አለ የኢትዮጵያ መድሀኒት ፈንድ ኤጀንሲ።

መድሀኒቶቹ ለትራኮማና መሰል በወረርሽኝ መልክ የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ መሆናቸውንም ኤጀንሲው አስታውቋል።

ከእነዚህም ውስጥ 90 በመቶ የሚሆኑት አስቀድሞ ለመከላከል የሚረዱ መሆኑን የኤጀንሲው የኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አድና በሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

መድሀኒቶቹ በሁለት ዙር በኤጀንሲው 17 ቅርንጫፎች አማካኝነት ችግሩ ጎልቶ በሚስተዋልባቸው በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በኦሮሚያ፣ በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ሀረሪ ክልሎች በተመረጡ ወረዳዎች መሰራጨታቸውንም ወይዘሮ አድና ገልጸዋል።

ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement