ቡና ጠጡና “ዕድሜ ጥገቡ”

                                                               

አንዲት ስኒ ቡና! አቦል ካለበለዚያም እስከ በረካው – የብዙ ሰው ሱስና የለት ተለት ቀጠሮው ነው። በተለይ በጠዋት “ፉት” የተባለች እንደሁ አህ!!! መልካም ቀን ተጀመረ ማለት ነው…
አንድ ሰሞኑን የወጣ አዲስ የጥናት ሪፖርት ደግሞ “ምን ቀን ብቻ? ዕድሜ ሙሉ እንጂ!” ይላል። በቀን ሦስት ስኒ ቡና የሚያጣጥሙ ሰዎች ከማይጠጡቱ ለተሻለ የዘመን ርዝማኔ እንዲሁ እንዳጣጣሙት ይኖራሉ፡፡
ሳይንቲስቶቹ ጥናቱን ያደረጉት ዕድሜአቸው ከ35 ዓመት በላይ በሆነ ቁጥራቸው ከግማሽ ሚሊየን በበዛ በአሥር የአውሮፓ ሃገሮች ውስጥ በሚኖሩ ጤናማ ሰዎች ላይ መሆኑን ሪፖርታቸው አሳይቷል።
“ባንዲት ስኒ ቡና ዋጋዋ ባነሰ፣ (የዛሬን አያድርገውና) ስንት ዕድሜ ረዘመ ስንቱ ሰው ታደሰ።” ብሎ ይፅፍ ይሆን ጠቃሽ?! ለማንኛውም “ቡና ጠጡ!”

ምንጭ:- ቪ ኦ ኤ(VOA)

 

Advertisement