በቆሎ ለቆዳ እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ

ወቅቱ ክረምት እንደመሆኑ በሀገራችን በአብዛኛውን ጊዜ የሚዘወተረው በቆሎ አስገራሚ የጤና በረከቶች እንዳሉት ይነገርለታል።

ታዲያ ይህ በብዛት በዓለማችነ ላይ ለምግብነት የሚውለው በቆሎ በርከት ያሉ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በቆሎ የፕሮቲን፣ የስብ እና  የአንቲኢክሲደንት መገኛ  መሆኑ እንዲሁም በካርቦሀይድሬት የበለጸገ በመሆኑ ለጤናችን እጅጉን ጠቀሜታ አለው።

በቆሎ ለቆዳ እና ለጸጉር ያለው ጠቀሜታ

በቆሎ በውስጡ በርካታ ቪታሞኖችን በመያዙ ለቆዳ እና ለጸጉር ጠቀሜታ እንዳለውም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በቆሎ ለቆዳ ውበት እና ጤነነት

በቆሎ መውስጡ ቤታ ካሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር በመያዙ ለቆዳችን ጤንነት እጅጉን ጠቃሚ ያደርገዋል።

እንዲሁም በበቆሎ ውስጥ የሚገኙት ቪታሚን C እና ላይኮፒን ንጥረ ነገሮች በጸሃይ ብርሃን አማካኝነት በቆዳችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት እንደሚከላከልልንም ተነግሯል።

ስለዚህም በቆሎን አዘውትረን ስንመገብ ከምግብነት ባለፈ የቆዳችንን ውበት እና ጤንነት እየጠበቅን መሆኑንም ልብ ልንለው የሚገባ ነው።

በቆሎ  ለጸጉር ጥንካሬ እና ውበት

በቆሎ ከጤና ባለፈ በውስጡ ባለው ንጥረ ነገሮች አማካኝነት የጸጉር መበጣጠስ፣ መነቃቀልን እና የጸጉር ድርቀትን ለመከላከል ይረዳናል።

በተጨማሪም በቆሎ፦

የምግብ መፈጨጥ ስርዓታችንን ያፋጥናል።

ደም ማነስን ይከላከላል።

ሰውነታችን ህይል እንዲያገኝ ያደርጋል።

ክብደትን ለመጨመር፦ የሰውነታቸው ክብደት እንዲጨምር ለሚፈልጉ ሰዎች።

ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊትን ይከላከላል።

ጤናማ እና የተስተካከለ የዓይን እይታ እንዲኖረን ይረዳናል።

ካንሰርን ይከላከላል።

የመርሳት ችግር/ Alzheimer/ ይከላከላል።

ለልብ ህመህ እንዳንጋለጥ ይረዳናል።

ምንጭ፦ healthdigezt.com

 

Advertisement