በዳይፐር የሚመጣ ቁስለት /Diaper rash/

ዳይፐር ራሽ /Diaper rash/ የህፃናት ቆዳን የማቃጠል ሁኔታ ሲሆን በዋነኝነት በሰገራና በሽንት አማካኝነት የሚከሰት ነው፡፡

የረጠበ ዳይፐር እና ለረጅም ግዜ ከቆዳ ጋር በቀጥታ ሲነካካ የሚፈጠር ነው፡፡
ምልክቶቹ፡-
-ዳይፐር የሚደርስበት ቦታ ላይ መቅላት፡ የቆዳ ቀለም መቀየር፡ትንንሽ እብጠቶች መኖር
-የቆዳ መድረቅ ወይም መላጥ
-ትንንሽ ውሃ የቋጠረ ቆዳ መታየት
-በአካባቢው ላይ የሙቀት ስሜት መኖር
ጠቃሚ ምክሮች
-የህፃኑን ዳይፐር ቶሎ ቶሎ መቀየር ማቃጠል እንዳይኖር ያደርጋል፡፡
-ህፃኑ ጠጣር ምግቦችን ከጀመረ ለምግቦቹ አለርጂ መሆን አለመሆኑን በአግባቡ ማረጋገጥ
-ራሹ እስኪጠፋ ከፕላስቲክ የተሰሩ ፓንቶችን አለመጠቀም
-ሽታ ያላቸውን ሣሙናዎች አለመጠቀም
-የእናት ጡት ወተትን በደንብ መስጠት
-ዳይፐር የሚያርፍበትን አካባቢ በአግባቡ ለብ ባለ ውሃና ሽታ በሌለው ሳሙና ማጠብና ማድረቅ
-ሁል ግዜ ንፁህ ቫዝሊን መጠቀም

ከ ዶክተር አለ!

 

Advertisement