የጨጓራ ህመም ሊከሰትባቸው ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል
1. ባክቴርያ
2. ከፍተኛ አልኮል መጠጦችን መውሰድ
3. ለረዥም ግዜ የሚወሰዱ አንዳንድ መድሃኒቶች
4.ከልክ ያለፈ መጨናነቅ
5.የመመገቢያ ሠአትን ጠብቆ አለመመገብ
የጨጓራ ህመምን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም እንችላለን
1.ዝንጅብል
አነስተኛ የዝንጅብል ክፍል ወስዶ ከምግብ በፊት መውሰድ የምግብ ልመትን ያፋጥናል በተጨማሪም የጨጓራ ባክቴሪያን ያክማል፡፡
2.እርጎ
በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሠት የጨጓራ ህመም ተመራጭ ነው፡፡
3.ድንች
ግማሽ ብርጭቆ የድንች ጁስን በቀን 3 ጊዜ ምግብ ከመመገብ 15 ደቂቃ በፊት መጠጣት
4.ቆስጣ እና ካሮት
የቆስጣ ጁስ እና የካሮት ጁስን በመደባለቅ መጠጣት
5.ውሃ
በቀን ከ8-10ብርጭቆ ውሃ መጠጣት
6.በፆም ወቅት ፍሬሽ የሆኑ የፍራፍሬ ጁሶችን መጠቀም ለምሳሌ ወይን ብርቱካን አፕል ፓፓያ…
7.ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ አለመመገብ ምክንያቱም ብዙ ምግብ በአንድ ጊዜ መመገብ የምግብ ልመትን ስለሚያዘገይ ትንሽ ትንሽ ምግብ ሠአትን ጠብቆ መመገብ
8.ሁል ጊዜ በባዶ ሆድ የሞቀ ውሃ መጠጣት
9.በአንድ ገበታ ላይ የተለያዩ ምግቦችን አደባልቀው አለመመገብ
10.ከመተኛቶ 2 ሠዓት በፊት እራት መመገብ
11.በቫይታሚን ቢ12 እና አይረን የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ
12.ስጋና የስጋ ተዋፅዎ መቀነስ በተለይ ለእራት አለመጠቀም
13.አልኮል ሲጃራና ጫትን አለመጠቀም
14.ቡናና ሻይ መቀነስ
14.ኬክ እና በፋብሪካ የተቀነባበሩ ምግቦችን አለመጠቀም
15.በሀኪም ያልታዘዙ መድሀኒቶች አለመውሰድ
16.ቅመማ ቅመም መቀነስ
ምንጭ: ጤናችን