የፊት ቆዳን ሊጎዱ የሚችሉ 7 ልማዶች

                                                                           

1) ከልክ በላይ መታጠብ

በተደጋጋሚ እጥበት ምክንያት የሚከሰትን ድርቀት ለመከላከል ቆዳችን ከልክ በላይ ዘይት መሰል ነገር ለማምረት ግዴታ ውስጥ ስለሚገባ ነው፡፡ ሜክአፕ፣ ሰንስክሪን እና መሰል መዋቢያዎችን የማትጠቀሙ ከሆነ እና ያን ያህል ላብ ፊታችሁ ላይ ከሌለ ምንም አይነት ማፅጃ ሳትጠቀሙ ለብ ባለ ውሃ ብቻ ፊታችሁን ማታ ማታ ታጠቡ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ቆዳችሁ ምንም አይነት መዋቢያ የማይጠቀምበት እረፍት መስጠትም መልካም ነው፡፡
2) ከልክ በላይ የጋለ ውሃ መጠቀም
ሞቃት ውሃ የፊታችንን ቆዳ ቀዳዳ ክፍት ያደርጋል፣ ቀዝቃዛ በሌላ በኩል ይዘጋል የሚል የተሳሳተ አመለካከት አለ፡፡ እውነታው ግን ፊታችን ላይ የሚገኙ ቆዳዎች ራሳቸውን የመክፈትም ሆነ የመዝጋት አቅም የላቸውም፡፡ እንደውም በሞቃት ውሃ ከልክ በላይ ቆዳችሁን በማጠብ ከፍተኛ ድርቀት ወይም አላስፈላጊ የሆነ ከፍተኛ የ‹ሴበም› ምርትን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የሚመከረው ለብ ያለ ውሃ መጠቀም ነው፡፡
3). ከልክ በላይ ‹ስክራብ› ማድረግ
የፊት ቆዳ ላይ የሚገኙ የሞቱ ህዋሶችን ቀርፎ በተለያየ መንገድ ማንሳት (ስክራብ) ተገቢ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይሄም በልኩ መሆን መቻል አለበት፡፡ እነዚህን ህይወት የሌላቸው ህዋሶች ለማስወገድ ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም ይመከራል፡፡ ከስኳር እና ከፍራፍሬዎች የሚገኝ አሲድ ተመራጭ ቆዳን ‹‹ስክራብ›› ማድረጊያ ናቸው፡፡ ቢበዛ ቢበዛ በሳምንት ሁለት እና ሶስት ጊዜ ብቻ ስክራብ አድርጉ፡፡ ስክራብ በምታደርጉበት ወቅት ቆዳችሁ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳይደርስ ከመታጠቢያ ፎጣ ይልቅ ጣታችሁን ተጠቀሙ፡፡
4). በበቂ ሁኔታ አለመታጠብ
የፊት ቆዳን በአግባቡ አለመታጠብ የፊት ቆዳ ቀዳዳዎች እንዲደፈኑ እና ድርቀት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
5). ፊት እስከሚደርቅ መጠበቅ
ፊታችሁን ከታጠባችሁ በኋላ ወዲያውኑ እርጥበቱ ሳይጠፋ ፊታችሁን ለማለስለስ የምትጠቀሟቸውን መዋቢያዎች ተቀቡ፡፡ ፊታችሁ ከደረቀ በኋላ መዋቢያዎችን መቀባት የተቀባችሁት ማንኛውም ነገር የቆዳ ቀዳዳዎች ዝግ ስለሚሆኑ ወደ ውስጥ ለመግባት ይቸገራል፡፡ 
6). ተፈጥሮዊ ያልሆኑ መዋቢያዎችን አለመጠቀም
ቀላል እና ተፈጥሯዊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን የያዙ የፊት ቆዳ ማፅጃዎችን መጠቀም፡፡ ከዚህ ውጪ ውድ የሆኑ በፍጹም ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የፊት ቆዳ ማፅጃዎችን መጠቀም አይመከርም፡፡
7) ተፈጥሯዊ ዘይት ነክ ማፅጃዎችን መጠቀም
ጥሩ የቆዳ ማፅጃ ዘይቶች ቆዳ ቀዳዳ ውስጥ የሚገኙ ቆሻሻዎችን እንዲሁም ባክቴሪዎችን ያፀዳሉ፡፡ የተጎዳ ቆዳን ለማከም ይረዳሉ፡፡ በመሆኑም ተፈጥሯዊ የሆኑ የአትክልት ዘይት ይዘት ያላቸውን ማፅጃዎች ተጠቀሙ፡፡እንደዚህ አይነት ማፅጃዎችን በቀላሉ ማግኘት የማትችሉ ከሆነ እንኳ ጥራት ያላቸውን የአልሞንድ እና ሱፍ ዘይቶችን እንድትጠቀሙ ይመከራል፡፡ 

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement