የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት

                                

የምግብ መመረዝ ወይንም የአንጀት ቁስለት የምንለው የሕመም ዓይነት የሚከሰተው በቫይረስ፣በባክቴሪያ፣እና በፓራሳይት አማካኝነት የተበከለን ምግብ በምንመገብበት ወቅት ነው፡፡
እነዚህ ተህዋስያን ምግብን በምናበስልበት ወቅት ሊበከሉ ስለሚችሉ ለምንመገበው ምግብ ንፅህና ጥንቃቄ መውሰድ ተገቢ ነው፡፡
 ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭንትን የሚጨምሩ ሁኔታዎች
• በእድሜ የገፉ ሰዎች ሕመም የመከላከል አቅማቸው እየተዳከመ ስለሚመጣ ተጋላጭ ይሆናሉ፣
• ነፍሰጡር ሴቶች ለአንጀት ቁስለት ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው
• ሕፃናት በሽታን የመከላከል አቅማቸው ጠንካራ ስላልሆነ በቀላሉ ለአንጀት ቁስለት ይጋለጣሉ
• ተጓዳኝ ሕመም ያለባቸው ሰዎች እንደ ስኳር ሕመም፣ጉበት ሕመም፣ በኤድስ የተጠቁ ሕሙማን ተጋላጭነታቸው የሰፋ ነው፡፡
 የአንጀት ቁስለት ምልክቶች
የምግብ መመረዝ/የአንጀት ቁስለት ሕመም ምልክቶች የተበከለ ምግብን ከተመገብን ከሰዓታት በኋላ የሚከሰቱ ሲሆን 
• ምልክቶቹም፡- ማቅለሽለሽ
ማስመለስ
ተቅማጥ
የሆድ ቁርጠት እና ትኩሳት ናቸው፡፡ እነዚህ ምልክቶች ለቀናት ሊቆዮ ይችላሉ፡፡
 ሐኪምዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነው?
• በተደጋጋሚ የሚያስመልስዎ ከሆነ
• ደም የቀላቀለ ትውከት ወይንም ተቅማጥ ከኖረ
• ከ3 ቀናት በላይ የሚቆይ ተቅማጥ ከኖረ
• ከፍተኛ የሆነ የሆድ ቁርጠት ካለ
• ከፍተኛ ትኩሳት ካለዎት
• ከፍተኛ የውሃ ጥማት፣የአፍ መድረቅ፣የድካም ስሜት፣ማዞር እና አነስተኛ የውኃ ሽንት ካለዎት ናቸው፡፡
 የምግብ መመረዝን ለመከላከል ምን ማድረግ ያስፈልግናል?
• የእጅን፣ ምግብ ማብሳያን እና መመገቢያ ቁሳቁሶችን ንፅሕና መጠበቅ
• ጥሬ /ያልበሰሉ/ ምግቦችን አለመመገብ
• ምግብዎን በፅዱ ቦታ ማስቀመጥና በተስማሚ የሙቀት መጠን ማብሰል
• ምግብዎን ለማቆየት ከፈለጉ በማቀዝቀዣ ውስጥ በማስቀመጥ እንዳይበከል መከላከል
• ምግብዎ የተበከለ ከመሰለዎ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው
የአንጀት ቁስለት/የምግብ መመረዝ/ ለሕፃናት፣ለነፍሰጡር ሴቶች፣በእድሜ ለገፉ እና ተጓዳኝ ሕመም ላላቸው ሰዎች አደገኛ እና ሕይወት እስከማጥፋት የሚያደርስ ሕመም ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥንቃቄዎች መተግበር ተገቢ ነው፡፡
የሕመም ምልክቶችም ከታየ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ቦታ በመሄድ መፍትሔ ማግኘት ይገባል፡፡

ምንጭ:- ጤናችን

Advertisement