ጨዋታ ህፃናትን ከማዝናናት ባለፈ የሚሰጣቸው በርካታ ጠቀሜታዎች::

                                   

ጨዋታ ህጻናት በተፈጥሮ የሚከውኑት ተግባር ሲሆን፥ ወላጆችም ይህንን ተግባራቸውን ሊያበረታቱት እንደሚገባ ይነገራል።

“ህጻናት በተፈጥሮ የመጫወት ፍላጎት አላቸው፤ ይህም በስነ ህይወት የተዘጋጀላቸው መርሃ ግብር ነው” የሚሉት የእንግሊዝ ቻሪቲ ፕሌይ ሊቀመንብር ኒኮላ በትለር፥ “ጨዋታ

ሰዎች እና ሌሎች አጥቢ እንስሳቶች አዳዲስ ነገሮችን የሚማሩበት መንገድ ነው” ብለዋል።

እንደ ወላጅ፥ ሁላችንም ለልጆቻችን ሙሉ በሙሉ የመጫወት ነጻነት መስጠት አለብን፤ ምክንያቱ ደግሞ ህፃናት ስለ ራሳቸው እና አካባቢያቸው ስላለው ዓለም የሚማሩት በጫተዋ ስለሆነ ነው።

በጫወታ ወቅት ህጻናት ነገሮችን የመረዳት አቅማቸው እና በራስ መተማመናቸው ቀጥለው በተዘረዘሩ አራት ነጥቦች ዙሪያ ይጨጠምራት ተብሏል።

1 አካላዊ፦ ጥንካሬ፣ ሚዛን መጠበቅ እና ሌሎች መሰል አካላዊ ክህሎቶችን በጫወታ ወቅት ያዳብራሉ።

2 ማህበራዊ እና ርህራሄ፦ ነገሮችን ማመዛዘን፣ ማዘዝ፣ ያላቸውን ከሰዎች ጋር መካፈል እና ተራ መጠበቅን ይማራሉ።

3 የፈጠራ እና የአስተሳሰብ አቅም፦ ህጻናት በጨዋታ ወቅት የሚያደርጓቸው ነገሮች የአስተሳሰብ እና የፈጠራ እቀማቸውን ይጨምራል።

4 ቋንቋ እና መግባባት፦ በጨዋታ ወቅት የህፃናት የመናገር፣ ትእዛዝ የመቀበል፣ ከሰዎች ጋር የመግባባት እና ሌሎች ክህሎቶች ይጨምራሉ።

ህፃናት ሁሌም በሚጫወቱበት ወቅት እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ክህሎቶች የማዳበር አቅማቸው ከእለት እለት እየጨመረ እንደሚሄድም ነው የሚነገረው።

በህፃናት ጨዋታ ውስጥ የወላጆች ሚና ምን መሆን አለበት…?

ከመመልከት ይልቅ አብሮ መጫወት

ህፃናት በሚጫወቱበት ጊዜ ከመመልከት ይልቅ አብሮ መጫወት ህጻናት በወደፊት ህይወታቸው የራስ መተማመንን እንዲያጎለብቱ እንደሚረዳቸውም የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ።

በጨዋታ ወቅት ህፃናት የመሪነቱን ሚና እንዲይዙ ማድረግ

ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ቁጥጥራችንን ቀለል ማድረግ እና በጨዋታ ወቅት ህጻናት የሚወስኑትን ነገር ማክበር እንዲሁም ፍላጎታቸውን መጠበቅ ከወላጆች ይጠበቃልም ተብሏል።

ይህም ህጻናት ነገሮችን ያለ ወላጆቻቸው ድጋፍ በራሳቸው እንዲያስተካክሉ አቅም ይፈጥርላቸዋል የተባለ ሲሆን፥ እንዲሁም በራስ የመተማመን አቅማቸውን ከፍ እንደሚያደርግም ተግልጿል።

ህፃናት እንዲጫወቱ የመጫወጫ ጊዜ እና ቦታ መስጠት

ህጻናት በሚጫወቱበት ጊዜ ማድረግ የፈለጉትን ነገሮች ሁሉ እንዲያደርጉ የሚያስችላቸውን ቦታ እና ጊዜ መስጠት በጨዋታ ወቅት ከወላጆች የሚጠበቅ መሆኑም ተገልጿል።

ምንጭ፦ www.huffingtonpost.co.uk

Advertisement