ቀይ ሽንኩርት ለጸጉር እድገት ያለውን ጠቀሜታ ያውቃሉ?
ብዙዎቻችን ቀይ ሽንኩርት ምግብ ለማዘጋጀት ከሚኖረው ፋይዳ ባለፈ ለጸጉር እድገት የሚረዱ ንጥረ ነገሮች መያዙን አንረዳም።
የቅርብ ጊዜ ጥናቶች ግን ቀይ ሽንኩርት የጸጉር መበጣጠስን ለመከላከልና የአዲስ ጸጉር እድገትን ለማፋጠን የሚረዳ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ቀይ ሽንኩርትን በምግብ መልክ አልያም በጭንቅላታችን ላይ ዘወትር መጠቀም እንደ ፎረፎር እና ሌሎች የጭንቅላትና ከጸጉር ጋር የተያያዙ በሽታዎችን ለመከላከል አይነተኛ ሚና ይጫወታል።
ቀይ ሽንኩርት በዘር ወይም ከእንክብካቤ ጉድለት የሚከሰት የጸጉር መበጣጠስን ለመቀነስና ካለጊዜ የሚመጣ የጸጉር ቀለም ለውጥ ወይም ሽበትን ለመከላከል ይረዳል ይላሉ ጥናቶቹ።
ጥሬ ሽንኩርትን በስሱ ክብ አድርጎ በመክተፍ ጸጉር ላይ ማድረግ የፀጉር እድገትን ለማፋጠን ይረዳል።
ቀይ ሽንኩርትን በጁስ መልክ በማዘጋጀት መጠቀምም የደም ዝውውርን በማቀላጠፍ የጸጉር እድገት እንዲፋጠን ያግዛል።
በሰልፈር የበለጸገው ሽንኩርት የጸጉር ቅንጣቶች እንዲቀጥኑ በማድረግ በርካታ ጸጉር እንዲኖረንም ከፍተኛ ጥቅም አለው።
ምናልባትም ጸጉርዎ እየተበጣጠሰ አልያም እድገቱ አዝጋሚ ሆኖ ከተቸገሩ እስኪ በየቀኑ ከማዕድ ቤትዎ አንድ ወይም ሁለት ራስ ሽንኩርት ለጸጉርዎ በማዋል ልዩነቱን ይመለከቱ።