ጨጓራ ህመምን የሚያሽሉ ምግቦች – Stomach Ulcer Natural Treatment

በጨጓራችን ውስጥ ያለው የአሲድ መጠን ሲጨምርና ሄሊኮባክተር (ኤች) ፓይሎሪ በተባለው ባክቴርያ ምከንያት ጨጓራችን ሊታመም ይችላል። ለዚህ ህመም የተለያዩ ህክምናዎች ሲኖሩ በተፈጥሮአዊ መንገድ የጨጓራ ህመምን ሊያሽሉ የሚችሉ እነዚህን የምግብ አይነቶች እንመልከት፦ 

  1.     ማር፦ ማር በውስጡ ከ200 በላይ ንጥረ-ነገሮችን ሲይዝ እንደ ኤች.ፓይሎሪ ያሉትን ባክቴሪያዎች የመዋጋት አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ የስኳር ህመም ከሌለብን ማርን በመመገብ የጨጓራ ህመማችንን ማከም እንችላለን።
  2.     ነጭ ሽንኩርት፦ ለብዙ በሽታዎች መድሃኒት እንደሆነ የሚታወቀው ነጭ ሽንኩርት የኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያ እንዳያድግ የማድረግ አቅሙ ከፍተኛ ነው። የነጭ ሽንኩርት ጣዕምን የማንወድ ሰዎች በመድሃኒት መልክ የተቀመመውን መጠቀም     እንችላለን። ነጭ ሽንኩርት በተፈጥሮው ደምን የማቅጠን ባህርይ ስላለው የታዘዙልን መድሃኒቶች ካሉ ሀኪምን ማማከር አስፋላጊ ነው።
  3.    ክራንቤሪ፦ ይህ በተለይ ለሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን ፍቱን መድሃኒት የሆነ ፍራፍሬ በመሆኑ ኤች.ፓይሎሪ ባክቴሪያን የመዋጋትም አቅም ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል። ክራንቤሪን በጁስ፣ በፍራፍሬ እና በመድሃኒት መልክ ልንወስድ እንችላለን       ሆኖም መጠኑን ካበዛን የሆድ ህመም ስለሚያስከትል በትነሹ ጀምረን መጠኑን መጨመር ይቻላል። ቀሪ ወሳኝ እና ዋና ዋና ነጥቦች በድረገፁ ላይ ተካተዋል ይመልከቷቸው።

 ምንጭ: Dr. David Williams

Advertisement