ስለ ጡትዎ ራስዎን ማወቅ መልእክት – Healthy Breasts

የጡት ካንሰር በአፍሪቃውያን-አሜሪካውያን ሴቶች መካከል በብዛት የሚታይ ካንሰር ሆንዋል። በጊዜው መፈተሽና አስፈላጊ የጡት ካንሰር እርዳታ ማግኘት በህይወት የመትረፉ ዕድል ሲያሻሽል ታይቷል።

1. ስጋትዎን ይወቁ

  • ስለ ቤተ-ሰብዎ የጤና ታሪክ ለመረዳት ቤተ-ሰቦችዎን ያነጋግሩ
  • በጡት ካንሰር ስለሚኖርብዎት ስጋት ሓኪምዎን ያነጋግሩ

2. ጡትዎን ይመርመሩ 

  • ከፍተኛ የስጋት ደረጃ ካሉት ከሆኑ ምን ዓይነት የማጣርያምርመራ እንደሚሻልዎት ለመረዳት ሓኪምዎን ይጠይቁ
  • በመካከለኛ የስጋት ደረጃ ካሉት ከሆኑ ዕድሜዎ ፵ ዓመት ከሞላ በኋላበየዓመቱ የማሞግራም ምርመራ ያድርጉ
  • ዕድሜዎ ፳ ዓመት ሲሞላ ቢያንስ በየሶስት ዓመቱ ፵ ዓመት ዕድሜ ሲሞላ ደግሞቢያንስ በየዓመቱ የክሊኒክ የጡት ምርመራ ያድርጉ
  • ስለሚደረግልዎት የማጣርያ ምርመራ ቀጠሮ እንዲያስታውስዎት በ komen.org/reminder ኢንተርነት ላይ ይመዝገቡ

3. እርስዎ የተለመደ ነው የሚሉትን ይወቁ

ከታች ከተዘረዘሩት ለውጦች ኣንዳችዋን ካዩ ሓኪምዎን ያነጋግሩ፤

  • እብጠት፣ የጠጠረ ነገር ወይም ውፍረት ከጡት ውስጥ ወይም ከብብት ስር 
  • እብጠት፣ የሙቀት ስሜት፣ ከጡትዎ ላይ ቀይ ወይም ጥቁር ምልክት
  • የጡት መጠን ወይም ቅርጽ ለውጥ
  • የቆዳ መጥለቅ ወይም መሸብሸብ
  • በጡት ጫፍ ማሳከክ፣ የሚቀረፍ ቁስል ወይም ሽፍታ
  • የጡትዎ ጫፍ ወይም ሌላ የጡትዎ ክፍል መዝቀጥ
  • ባልታሰበ ጊዜ በጡት ጫፍ የሚታይ ፈሳሽ
  • ከአንድ ቦታ ላይ የሚሰማ የማይለቅ አዲስ ሕመም

4. ጤናማ የአኗኗር ምርጫ ያድርጉ

  • ክብደትዎ ለጤናዎ አመቺ እንዲሆን ለማድረግ ይሞክሩ
  • በየቀኑ ከሚሰሯቸው ስራዎች በላይ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግይሞክሩ
  • የሚጠጡትን አልኮል መጠን ለመቀነስ ይሞክሩ
  • ከወር አደፍ ማቋረጥ በኋላ የሚጠቀሙበት ሆርሞን ለመቀነስ ይሞክሩ
  • ከተቻልዎት ሕጻንን ጡትዎን ማጥባት ይሞክሩ

 ምንጭ: komen.org

 <—–ምስሉን በትልቁ ለማየት ምስሉ ላይ ተጫኑ

 

 

Advertisement