ለጤናዎ ­ የቫይታሚን ሲ ተፈጥሯዊ ምንጮች – Natural Sources For Vitamin “c” to Keep out Body Healthy.

                                              

ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የህክምና ባለሙያዎች በማማከር ጤናዎን በቤትዎ ይጠብቁ ይንከባከቡ ከበሽታ ይከላከሉ፡፡

አስኮርቢክ አሲድ የሚል መጠሪያ ያለው ቫይታሚን ሲ ለሰው ልጅ እድገት እና የተስተካከለ ጤነነት ጠቃሚ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች ውስጥ ይመደባል።

ከአንቲ ኦክሲዳንት ንጥረ ነገሮች ውስጥ የሚጠቃለለው ቫይታሚን ሲ በሽታ የመከላከል እቅማችንን የሚጨምር ሲሆን፥ በተጨማሪም በሰውነታችን ውስጥ ላሉ የሴሎችን እድገት ጠቀሜታ አለው።

እንዲሁም ለልብ ህመምን፣ ለደም ግፊት፣ ለጉንፋን፣ እና አስም በቀላሉ እንዳንጋለጥ ይረዳናል ።

ከ0 እስከ 6 ወር ያሉ ህጻናት በቀን ውስጥ እስከ 40 ሚሊግራም፣ 
ከ7 እስክ 12 ወር 50 ሚሊግራም፣ 
ከ1 ዓመት እስክ 3 ዓመት 15 ሚሊግራም፣ 
ከ4 እስከ 8 ዓመት 25 ሚሊግራም፣ 
ከ9 እስከ 13 ዓመት 45 ሚሊ ግራም፣ 
ከ14 እስክ 18 ዓመት ወንድ 75 ሚሊ ግራም፣ ሴት 65 ሚሊግራም፣ 
ከ19 ዓመት በላይ ያሉ ወንድ 90 ሚሊ ግራም፣ ሴት 75ሚሊግራም፣ ነብሰ ጡር ሴቶች 85 ሚሊ ግራም፣ ጡት የሚያጠቡ ሴቶች 120 ሚሊግራም ቫይታሚን ሲ ቢያገኙ መልካም ነው።

የቫይታሚን ሲ እጥረትም ለሰውነት ቆዳ በሽታ፣ የአፍ ውስጥ ህመም እንደ የመንጋጋ ችግር፣ የጥርስ ህመም እንዲሁም የመገጣጠሚያ አካላት ማላብ፣ የጸጉር መነቃቀል፣የአፍንጫ መድማት ወይም ነስር እና ሌሎች ተመሳሳይ ችግሮችን ሊያስከትልብን ይችላል።

ስለዚህም ቫይታሚን ሲ በየእለቱ ልናገኛቸው ከምንችለው የአትክልትና ፍራፈሬ አይነቶች በምግባችን ውስጥ በማካተት ጤንነታችንን በቀላሉ መጠበቅ እንችላለን።

ቫይታሚን ሲ በውስጣቸው የያዙ የምግብ አይነቶች፦

ፓፓያ

ፓፓያ ቫይታሚን ሲ በውስጡ እንዳለው ጥናቶች ያመላክታሉ፤ በ100 ግራም ፓፓያ ውስጥም 62 ሚሊግራም
ቫይታሚን ሲ ይገኛል።
ይህ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በቀን ውስጥ ያስፈልገዋል ከተባለው የቫይታሚን ሲ መጠን 75 በመቶ መሆኑ ነው።
ፓፓያ በተጨማሪም ቫይታሚን ኤ በውስጡ ያለው ሲሆን፥ እንደ ቤታ ካሮቲን፣ ፎሌት፣ ፋይበር፣ ማግኒዥየም እና ፕሮቲን ያሉ ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።

ሚጥሚጣ

ሚጥሚጣ በውስጡ የቫይታሚን ሲ ንጥረ ነገር ያለው ሲሆን፥ ይህም በ100 ግራም ሚጥሚጣ ውስጥ 80 ነጥብ 6 ሚሊግራም ቪታሚን ሲ ማግኘት እንችላለን።
ይህም በእለት ከሚያስፈልገን የቫይታሚን ሲ መጠን 97 በመቶ ነው።
ሚጥሚጣ ከቫይታሚን ሲ በተጨማሪ፥ ቫይታሚን ኬ፣ ቢ6 እና ኢ እንዲሁም ፖታሲየም፣ ፎሌት ማግኒዥየም፣ አልፋ እና ቤታ ካሮቲን፣ ሉቴዪን እና ሌሎች ለጤና ጠቃሚ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን ይዟል።

ጎመን

ከ100 ግራም ጎመን 89 ነጥብ 2 ሚሊ ግራም ቫይታሚን ሲ ማግኘት የምንችል ሲሆን፥ ይህም በቀን ከሚያስፈልገን የቫይታሚን ሲ መጠን ጋር በመቶኛ ሲሰላ 107 በመቶ ነው።

እንጆሪ

እንጆሪም በ100 ግራም ውስጥ 58 ነጥብ 8 ሚሊግራም ቫይታሚን ሲ የያዘ ሲሆን፥ ይህም በቀን ከሚያስፈልገን ውስጥ 71 በመቶ ነው።

ብርትኳን

በ100 ግራም ብርትኳን ውስጥ 53 ነጥብ 2 ሚሊ ግራም ቫይታሚን ሲ ማግኘት እንችላለን።
ይህም በቀን ውስጥ ከሚያስፈልገን የቫይታሚን ሲ መጠን ጋር በመቶኛ ሲሰላ 64 በመቶ መሆኑ ነው።
በተጨማሪም ብርትኳን በርካታ የጤና ጠቀሜታዎችን ስላሉት አዘውትረን ብንጠቀመው ይመከራል።

አናናስ

አናናስ በ100 ግራም ውስጥ 47 ነጥብ 8 ሚሊ ግራም ቫይታሚን ሲ ይዟል።
ይህም በቀን ውስጥ ከሚያስፈልገን የቫይታሚን ሲ መጠን 58 በመቶ መሆኑን ተመራማሪዎች ተናግረዋል።

ጥቅል ጎመን

ጥቅል ጎመንም ልክ እንደሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች ሁሉ በ100 ግራም ውስጥ 48 ነጥብ ሁለት ሚሊግራም ቫይታሚን ሲ የያዘ ሲሆን፥ ይህም በቀን ውስጥ ያስፈልገናል ከተባለው መጠን ጋር ሲነጻጸር 58 በመቶ ይሆናል።

ምንጭ :- ጤናችን

Advertisement