የአሜሪካ የካንሰር ሶሳይቲ ባጠናው ጥናት በቀን ውስት ከሶስት እስከ አምስት ሰዓት ብቻ የሚተኙ ወንዶች በፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው 55 በመቶ ነው ብሏል፡፡
በቀን ለስድስት ሰዓታት የሚተኙትም፣ ቢሆኑ የመያዝ እድላቸው 29 በመቶ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡
የእንቅልፍ እጥረት የእንቅልፍ እና የመንቃት ኡደትን የሚቆጣጠረውን ሜላቶኒን ሆርሞን ያጠፋዋል ወይም እንዳይመነጭ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ዝቅተኛ የሜላቶኒን መጠን ዲ ኤን ኤ መመረትን ይቀንሳል ዘር ፍሬ ምክነትንም ያስከትላል ነው ያለው ጥናቱ፡፡
በየቀኑ በቂ እንቅልፍ መተኛት ጥሩ እረፍት ለማድረግ ብቻ ሳይሆን ህይወትን ለማርዘምም እድል ይፈጥራል፡፡
ከ65 ዓመት በታች የሆናቸው ወንዶች በቀን ውስጥ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት መተኛት ተገቢ ነው ከሚባለው የእንቅልፍ የጊዜ ወሰን አሳጥረው የሚተኙ ከሆነ ለፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡
የአሜሪካ የካንሰር ሶሳይቲ በጉዳዩ ላይ ረጅም ጊዜ የወሰደ ጥናት አካሂዷል፡፡
ተቋሙ ጥናቱን በሁለት ዘርፍ ያካሄደ ሲሆን የመጀመሪው ከ1950 እስከ 1972 ባለው ጊዜ ውስጥ፥ 407 ሺህ ወንዶችን ሲሆን በሁለተኛው ጥናት ደግሞ ከ1982 እስከ 2012 ባለው ጊዜ ውስጥ 416 ሺህ ወንዶችን በጥናቱ አካቷል።
እነዚህ ወንዶች ጥናቱ ሲጀመር ሁሉም ከካንሰር ነጻ ነበሩ፡፡
ሆኖም ከመጀመሪያው ጥናት ውስጥ 1 ሺህ 500 ወንዶች ከሁለተኛው ጥናት ደግሞ 8 ሺህ 700 ወንዶች በጥናቱ የክትትል ጊዜ ውስጥ በፕሮስቴት ካንሰር ህመም ሞተዋል ይላል ጥናቱ፡፡
ከዚያም በኋላ ተመራማሪዎች የወንዶችን የመኝታ ሰዓት ማጥናት ጀመሩ፤ በመጀመሪያዎች የስምንት ዓመታት ክትትልም እድሜያቸው ከ95 ዓመት በታች የሆኑት እና ከሶስት እስከ አምስት ሰዓት ብቻ በቀን ውስጥ የሚተኙ ወንዶች በፕሮስቴት ካንሰር ተይዘው የሞት እድላቸው 55 በመቶ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
65 ዓመት እና በላይ እድሜ ያላቸው ወንዶች ግን በቀን ውስጥ በሚተኙት ጊዜ ማጠር እና መብዛት ምክንያት ምንም ኣይነት የህመሙ ለውጥ አልታየባቸውም፡፡
በአሜሪካ ወንዶች ዘንድ ከቆዳ ካንሰር ቀጥሎ የፕሮስቴት ካንሰር አደገኛ ሲሆን በየዓመቱም በዚህ ህመም 27 ሺህ ወንዶች ይሞታሉ፡፡
የጥናቱ መሪ እና የአሜሪካ የካንሰር ሶሳይቲ የተላላፊ በሽዎች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ሱሳን ጋፕሰቱር እንደሚሉት በቂ እንቅልፍ መተኛት በተለይም የእንቅልፍ ፋውንዴሽን ካስቀመጠው በቀን ውስጥ ከሰባት እስከ ስምንት ሰዓት መተኛት ለፕሮስቴት ካንሰር የመጋለጥ እድልን ይቀንሳል፡፡
ዶክተር ጋፕስቱር አክለውም ሌሎች ተጨማሪ ስነህይወታዊ ምርምሮች በዚህ ጉዳይ ላይ ማካሄድ እንደሚስፈልግ ጠቁመው እስከዚያው ድረስ ግን ወንዶች በቂ እንቅልፍ እንዲተኙ መክረዋል፡፡
ምንጭ፡- dailymail