የጉበት መመረዝ 5 መነሻዎች – Causes for Liver Poisoning

                                      

(በዳንኤል አማረ ኢትዮጤና)
ጉበትዎን ሊጎዱ ስለሚችሉ ነገሮች ግንዛቤዎትን በመጨመር ጉበትዎን ከሚጎዱ ነገሮች አስቀድመው እንዲከላከሉ የዶክተር አለ! 8809 ሀኪሞችን ደዉለው ምን ማድረግ እንደሚገባዎ ያማክሯቸው፡፡
የጉበት መመረዝ የሚመጣው መርዛማ ነገሮች በጉበት ውስጥ በሚጠራቀሙበት ጊዜ ነው። ዋናው የጉበት ጥቅም መርዛማ ነገሮችን ከሰውነታችን ውጪ ጠራርጐ ማውጣት ነው ለነዚህ መርዛማ ነገሮች ለረጂም ጊዜ በምንጋለጥበት ጊዜ ከባድ የጉበት ጉዳት ያመጣሉ።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ከሚሆኑት መካከል አንድ መድሃኒቶች ናቸው መድሃኒት በምንወስድበት ጊዜ ጉበታችን በመድሃኒቱ ውስጥ ያሉ ንጥረ ነገሮችን ይሰባብራቸዋል ከዚያም በሀሞት እና ሽንት አማካይነት ከሰውነታችን ውጪ ያስወግዳቸዋል በመጨረሻም ተረፈ ምርቶች ይመረታሉ።
እነዚህ ተረፈ ምርቶች በጉበት ውስጥ ይቆያሉ መድሃኒቶቹ ኬሚካል ስለሆኑ ለጉበት መርዛማ ይሆናሉ ከዚያም የጉበት መቅላት/መቆጣት ያስከትላሉ በመጨረሻም ጉበት ስራውን ያቆማል ለህይወትም አስጊ ደረጃ ላይ ያደርሰናል።
ጉበትን የሚጐድ መርዛማ ነገሮች እነሆ፦
1. አልኮል መጠጦች
አልኮል የተለመደ የጉበት መመረዝን የሚያመጣ ነው። ከ1-2 ብርጭቆ ወይን ወይም ቢራ በሳምንት በቂና ለጤና ተስማሚ ነው ነገር ግን በብዛት የሚጠጡ ከሆነ ጉበትዎን እየጐድት መሆኑን ማወቅ አለብዎት ከብዙ ጊዜ ቆይታ በኃላ የጉበት ሄፓታይተስ ያስከትላል። በዚሁ ከቀጠለ ደግሞ ጉበት ስራውን ያቆማል ይህም ሁኔታ ገዳይ ነው።
2. ለህመም ማስታገሻ የሚወሰድ መድሃኒቶች
እነዚህ መድሃኒቶች ቀላል የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች ሲሆኑ ያለ መድሃኒት ማዘዣ የምንገዛቸው ናቸው። ለረጂም ጊዜ ወይም በብዛት ስንወስዳቸው ድንገተኛ የሆነ ከፍተኛ መጠን ያለው መርዝ ጉበት ላይ እንዲፈጠር ያደርጋል ይህም የመርዝ መጠን ጉበት ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ይሆንበታል።
ማወቅ ያለብን ሌላው ጉዳይ እነዚህን መድሃኒቶች እንደ አልኮል ካሉ ሌሎች መርዛማ ነገሮች ጋር አብሮ መውሰድ ይህን ጉዳት በእጥፍ ይጨምረዋል።
ይህን ችግር ከሚያስከትሉ መድሃኒቶች መካከል፦ አስፕሪን፣ አይቡፕሮፊን፣ አሲታሚኖፊሊን፣ ፓናዶል እና ናፕሮክሲን ሲሆኑ በተለያዮ የመድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣኖች እንደሚገልጽት ዋነኛውና የመጀመሪያው የጉበት ስራ ማቆም መነሻ ምክንያቶች መድሃኒቶች እንደሆኑ ተናግረዋል።
3. በመድሃኒት ማዘዣ የሚታዘዙ መድሃኒቶች
ማዬ ክሊኒኰች እነዚህ መድሃኒቶች የጉበት መመረዝን ያስከትላሉ ይሉናል፦
ኦጉመንቲን፣ ሀሎቲን፣ አይሶኒያዛይድ፣ ቫልፕሮክ አሲድ ፌናይታዮን፣ አዛታዮፕሪን፣ ኒያሲን፣ ሎቫስታቲን፣ ፕራቫስታቲን፣ ሲምቫስታቲን፣ ፍሉቫስታቲን፣ ሮሱቫስታቲን፣ ኬቶኰናዞል እና አንዳንድ የፀረ ባክቴሪያና ቫይረስ መድሃኒቶች ናቸው። በአሜሪካ በአመት ውስጥ እስከ 100,000 ሰዎች በነዚህ መድሃኒቶች በመመረዝ ይሞታሉ።
4. ለመድሃኒትነት የሚጠቅሙ ተክሎችና የምግብነት ይዘት ያላቸው ተጨማሪ ምግቦች
በብዛት ስንወስዳቸው የጉበት ጉዳት የሚያመጡ በተፈጥሮ የሚገኙ ለመድሃኒትነት የሚጠቅሙ ተክሎች አሉ። በተለይ በሀገራችን የባህል መድሃኒት የምንላቸው በእርግጥ እነዚህ ተክሎች(መድሃኒቶች) ለመድሃኒትነት ሊያገለግሉ ይችሉ ይሆናል ትልቁ ችግራቸው ምን ያህል መጠን መወሰድ እንዳለባቸው አለመታወቁ ነው። ከነዚህ መድሃኒቶች መካከል የሚጠቀሱት፦ ካስካራ፣ ቻፓራል፣ ኮምፍሬይ፣ ካቫ፣ ኢፌድራ ናቸው።
በተጨማሪም አንዳንድ ተጨማሪ ምግቦች በብዛት ሲወሰድ የጉበት መመረዝን ያስከትላሉ። በተለያዮ አጋጣሚዎች ህፃናት እነዚህ ምግቦች ከረሚላ ስለሚመስላቸው ይመገቧቸዋል።
5. በገበያ ላይ የሚሸጡ እና የኢንደስትሪ ኬሚካሎች
በብዛት በገበያ ላይ እና በተለያዮ ኢንደስትሪዎች የሚገኙ ኬሚካሎች የጉበት ጉዳት ሊያመጡ ይችላሉ። በጣም የታወቁ ይህን ችግር የሚያስከትሉ ኬሚካሎች እነዚህ ናቸው፦
★ክሎሪኔትድ ሶልቨንት
★ካርበን ቴትራክሎራይድ( በደረቅ እጥበት የምንጠቀምባቸው)

ምንጭ፡- ጤናችን

 

Advertisement