በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት ምን እናድርግ? በተለይ እንደ አዋሳ፣ አዳማና ሌሎች በስምጥ ሸለቆ የሚገኙ አካባቢዎች

                                           

የመሬት ዉጫዊው ክፍል በተለያዩ ቅርፊት መሰል አካላት(plates) የተሸፈነ ነዉ፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት ዉፍረት በአማካይ ከ(20-60) ኪ.ሜትር ወደ መሬት ስር ይዘልቃል፡፡ እነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት በመካከላቸዉ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ የኃይል መጠራቀም ይፈጥራል፡፡ የኃይል መጠራቀሙም እየጨመረ ይሄድና የአለቱ አካል ሊሸከመዉ ከሚችለዉ አቅም በላይ ሲሆን ይደረመሳል፡፡ ይህ በከፍተኛ ጫና ታፍኖ የነበረ ኃይል በድንገት ሲያፈነግጥ የሚወጣዉ ከፍተኛ ኃይል በመሬት የላይኛዉ ቅርፊት አካል ላይ በሞገድ መልክ በፍጥነት ይሰራጫል፡፡ የዚህን ጊዜ የመሬት መንቀጥቀጥ ተፈጠረ ወይም ተከሰተ እንላለን፡፡ የነዚህ ቅርፊት መሰል አካላት እንቅስቃሴ ሁኔታ እና መጠን እንደየአካባቢዉ ይለያያል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ ጥናት ሴስሞሎጂ (Seismology) ይባላል፡፡ ቃሉም የግሪክ (Seismos) ሲሆን ትርጉሙም መንቀጥቀጥ ማለት ነዉ፡፡

እነዚህ ቅርፊት አካሎች(Plates) አንዱ ከሌላዉ የሚለይበት እጅግ በጣም ረዥም የሆነ ስንጥቅ ይገኛል፡፡ ይህ ስንጥቅ የተለያዩ መዛነፎችን ይፈጥራል፡፡ ይህ አጠቃላይ ስንጥቅም የዝንፈት መስመር(fault line) ይባላል፡፡ በዝንፈት መስመር የሚለያዩ ቅርፊተ አካሎች(Plates) እጅግ ግዙፍ እንደመሆናቸዉ መጠን አንደኛዉ በሌላኛዉ ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው የማይቀር ነዉ፡፡ በመሆኑም እነኚህ የተለያዩ ቅርፊተ አካሎች እርስ በርሳቸዉ በተቃራኒ አቅጣጫ አንዱ ከሌላኛዉ ሊሸሽ ይችላል፡፡ ይህ ሁኔታ ቅርፊተ አካሎቹ እርስ በርሳቸዉ ተደጋግፈዉ የሚኖሩበትን መንገድ ስለሚያመክን በከፍተኛ ጫና ምክንያት አለቶቹ ተያይዘዉ እንዲደረመሱ ሲያደረግ ታምቆ የቆየዉ ኃይል በማፈንገጥ የሚለቀዉ ኃይል ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ ይፈጥራል፡፡ ከዚህ ማዕከላዊ ቦታ የሚነሳዉ ከፍተኛ ሞገድ በሁሉም አቅጣጫ በመሰራጨት እረጃጅም ስንጥቅ መስመሮችን እየሠራ በመቀጠል የላይኛዉን የመሬት ንጣፍ ገፅታ ያመሰቃቅላል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ የሚያስከትለዉ ዉድመት አደጋዉ የደረሰበት አካባቢ ያለዉ የመሬት አቀማመጥ፣ መንቀጥቀጡ የሚቆይበት ጊዜ እና መንቀጥቀጡ የሸፈነዉ ክልል ይወስነዋል፡፡ ህንፃዎች የተሠሩበት የንድፍ ዓይነት እና ለግንባታ ጥቅም ላይ የዋለዉ የቁስ ዓይነትም የአደጋዉን አስከፊነት ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል፡፡

የመሬት መንቀጥቀጥ በኢትዮጵያ

በሀገራችን ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያጠቃቸው ይችላሉ ተብለው የተለዩ አካባቢዎች አሉ ወይ? ብለን ብንጠይቅ አብዛኞቹ የሃገራችን ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ ከስምጥ ሸለቆ የራቁ አይደሉም፡፡ ምናልባት በሃገራችን ምዕራባዊ ክፍል ባህርዳር፣ ጎንደር እና ወለጋ አካባቢ ደህና ይሆናል፡፡ እንዲሁም በምስራቃዊው የሃገራችን ክፍል ጎባና ሮቤ ሊድኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ ውጪ ሌላው ከመሬት መንቀጥቀጥ እይታ ውጪ አይደለም፡፡ መቀሌን ብንወስድ የስምጥ ሸለቆ ጫፍ ላይ ትገኛለች፡፡ ወደታች ብንወርድ ወልድያ እና ደሴ ከስምጥ ሸለቆ  ጫፍ አይርቁም፡፡ ድሬዳዋና ሃረር ያሉበት ሁኔታ ብዙም ባይርቅም የተሻለ ነው፡፡ ጥፋት ሊደርስ የሚችል የመሬት መንጥቀጥ ያለው በምዕራባዊ ዳርቻ ነው፡፡ አሁን በማደግ ላይ ያሉት ከተሞች አዳማ፣ ሻሸመኔ እና ሃዋሳ ስምጥ ሸለቆ ውሥጥ ናቸው፡፡ የሚገኙት በጣም አሳሳቢ በሚባል ቦታ ላይ ነው፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ እና እሳተ ገሞራ በጣም የተቆራኙ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሊፈነዳ የሚችል እሳተ ገሞራን ክትትል ከተደረገበት አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል፡፡ በአካባቢው አየር(ጋዝ) እና አመድ መሰል ብናኝ ቅንጣጦች የሚስተዋሉ ከሆነ እንደ ጥቆማ ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም የሚፈጠረውን ንዝረት በማጥናት ሊፈነዳ የሚችልበትን ወቅት መገምገም ይቻላል፡፡ ባይፈነዳ እንኳን ለጥንቃቄ ዝግጅት ይደረጋል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥን ከተመለከትን ባልታሰበ ሰዓት ሊፈጠር የሚችል እውነታ ነው፡፡ በመሆኑም መጠኑን ፣ ጊዜውን እና ቦታውን ለመተንበይ በጣም ከባድ ነው፡፡

በሀገራችን ኢትዮጵያ የመሬት መንቀጥቀጥ ሊያጠቃቸው ይችላሉ ተብለው የተለዩ አካባቢዎች አሉ ወይ? ብለን ብንጠይቅ አብዛኞቹ የሃገራችን ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ ከስምጥ ሸለቆ የራቁ አይደሉም:: በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት አጀማመሩ ረጋ ያለ የሚመስል ንዝረት ቀደም ብሎ ሊሰማን ይችላል፤ ወዲያው በሰከንዶች ውስጥ ግን ወደ ለየለት ቀውጢ ሁኔታ የሚቀየር ሊሆን ይችላል፡፡ ከቆምንበትም አንስቶ ሊያፈርጠን ይችላል፡፡ ቤታችን ውስጥ ከሆንን በመጀመሪያ ቤታችን በትልቅ መኪና የተመታ ያህል ንዝረት ይሰማናል፡፡ በመቀጠልም በ2እና 3 ሰከንዶች ውስጥ ዋናውን መሬት መንቀጥቀጥ እናስተናግዳለን፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ እጅግ በጣም ከባድ ነው፡፡ ሂደቱ ፈጣን እና ቅፅበታዊ ስለሆነ ምንም እርምጃ ለመውሰድ አስቸጋሪ ይሆናል፡፡ በተቻለን መጠን ከመጮህ እና ከመረበሽ ተቆጥበን ሌሎችንም በማረጋጋት ሁኔታውን እራሳችንን ተቆጣጥረን ለማሳለፍ መሞከር አለብን፡፡ የመሬት መንቀጥቀጥ እና እሳተ ገሞራ እጅግ በጣም አጥፊ የሆኑ የተፈጥሮ አደጋዎች ናቸው፡፡ በተለይ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች የተከሰቱ ከሆነ የጉዳት መጠኑ በጣም ዘግናኝ ሊሆን ይችላል፡፡ መሬት መንቀጥቀጥ እና እሳተ ገሞራ የሚፈጠሩበትን ምክንያቶች ማወቅና ተገቢውን ምላሽ መስጠት በሰው፣ በንብረት እና በአካባቢያችን ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ለመቀነስ ይረዳል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎች

  • በመሬት መንቀጥቀጥ ወቅት በቤቶች ውስጥ ከሆንን እዛው ቤት ውስጥ በመቆየት በበር ማቀፊያዎች፣ በቤቱ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች በመሆን ልናሳልፍ ይገባል፡፡ ከመስኮት አካባቢ፣ ከመፅሐፍ መደርደሪያዎች፣ ከእሳት ምድጃዎች እና ከተሰቀሉ የመስታወት ፍሬሞች መንቀጥቀጡ እስኪያቆም ድረስ መራቅ አለብን፡፡
  • በአደጋው ወቅት በትልቅ አፓርታማዎች እና ህንፃዎች ውስጥ የምንገኝ ከሆነ የመሬት መንቀጥቀጡ እስከሚያቆም ድረስ በዛው በምንገኝበት ቦታ መቆየት አለብን፡፡ ሊፍቶችን ለመጠቀም በፍፁም መሞከር የለብንም ፤ ደረጃዎችም በመንቀጥቀጥ ወቅት ሊፈርሱ ስለሚችሉ ሁኔታው እስከሚያልፍ ድረስ መጠቀም የለብንም፡፡ በአደጋው ወቅት አለመንቀሳቀስን እንደ ህግ ብንወስደው ይመረጣል፡፡ በተቻለን መጠን የህንፃው ተሸካሚ የሆኑ ቋሚዎች አካባቢ ብንሆን ጉዳታችን ሊቀንስ ይችላል፡፡ ህንፃዎች ውስጥ እያለን የመሬት መንቀጥቀጥ በሚከሰትበት ጊዜ ህንፃው ካልፈረሰ በስተቀር ዋናው የአደጋ ምንጭ የሚሆኑት በላያችን ላይ ሊወድቁ የሚችሉት የተለያዩ ቁሳቁሶች እና አንዳንድ የግርግዳ ፍርስራሾች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከህንፃው ለመውጣት አመቺ ሁኔታዎች እስኪፈጠሩ ድረስ ባለንበት መቆየት አለብን፡፡
  • የጋዝ ምድጃዎችን እየተጠቀምን ከሆነ በመጀመሪያ የሚሰማንን ንዝረት እንደ ፍንጭ ተጠቅመን በቅፅፈት ልናጠፋው ይገባል፡፡
  • ከቤት ውጪ ከሆንን በፍጥነት ዛፎች፣ ህንፃዎች፣ የኤሌትሪክ ምሰሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱብን ከሚችሉ ነገሮች በመራቅ ገላጣ ቦታ ላይ መሆን አለብን፡፡
  • በአደጋው ሰዓት ህዝብ በበዛበት እና በተጨናነቀ ህንፃዎች ውስጥ ወይም መዝናኛ አካባቢዎች ከሆንን ሌሎች እንደሚያደርጉት  ወደ መውጫ በሮች መሮጥ ሳይሆን ያለብን፤ ሊወድቁብን የሚችሉ እቃዎች ወደ ሌሉበት ቦታ መሆን አለበት፡፡
  • አደጋው የተከሰተው መኪና እየነዳን ከሆነ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሰሶዎች፣ ዛፎች እና ሽቦዎች ሊወድቁብን ስለሚችሉ፤ ይህ ሁኔታ ሊደርስብን ወደ ማይችልበት ቦታ በመቆም ባለንበት መቆየት አለብን፡፡ ያለነው የቀለበት ማሳለጫ መንገዶች ውስጥ ከሆነ መንገዶቹ  ሊናዱብን ስለሚችሉ በፍጥነት ይህ ሊሆን ወደማይችልበት ገላጣ ቦታ ዳር ይዘን ሁኔታው እስኪያልፍ መጠበቅ አለብን፡፡
  • በመኪና ውስጥ እያለን የኤሌትሪክ መስመር ምሰሶዎች እና ሽቦዎች በመኪናችን ላይ ከወደቁ፤ ከመኪናው ለመውጣት በፍፁም መሞከር የለብንም፡፡ ሁኔታው እስከሚያልፍ በዛው መቆየት አለብን፡፡
  • አደጋው ሲፈጠርም ሆነ ካለፈ በኋላ ምንም አይነት ድልድዮችን በመኪና ለማቋረጥ መሞከር የለብንም፡፡ ምክንያቱም የሚገኙበት ሁኔታ በቋፍ ሊሆን ይችላል፡፡ በአደጋው ጊዜ የሚፈጠሩ የተለያዩ የመኪናም ሆነ ሌሎች የአላርም ድምፆች ሊረብሹንም ሆነ ሊያስደነግጡን አይገባም፡፡

መሬት መንቀጥቀጥ ካቆመ በኋላ ልንወስድ የሚገባን እርምጃ

  • ልክ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደቆመ በህይወት መትረፍ ከቻልን እና የተጎዳን ከሆነ የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ለራሳችን መስጠት ወይም ወደምናገኝበት ቦታ መሄድ፤ ደህና ከሆንን ደግሞ ለሌሎች ለመስጠት መሞከር አለብን፡፡ በራሳችንም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን ከባድ ከሆነ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለመዘዋወር መሞከር የለብንም፣ ምክንያቱም ሁኔታው በእንቅስቅሴ ምክንያት ሊብስ አልፎተርፎም ለሞት ሊያበቃ ይችላል፡፡
  • እንደ ሞባይል ስልክ እና ሬዲዮ ያሉ መገናኛዎች የሚሰሩልን ከሆነ እርዳታ ለማግኘት ጥሪዎችን ማድረግ አለብን፡፡
  • በፍርስራሽ ስር ተቀብረን በህይወት የምንገኝ ከሆነ የብቻችን ጥረት ላይሳካ ስለሚችል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም ሆኑ ሌሎች ሰዎች እስኪደርሱ ብንጠብቅ የተሸለ ነው፡፡ የድረሱልኝ ጥሪም ደጋግመን ማሰማት አለብን፡፡
  • የህክምና መርጃ ማዕከላት ከአደጋ በኋላ በተጎጂዎች ሊጨናነቁ ስለሚችሉ የምንፈልገውን እርዳታ ከባለሙያተኞች ለማግኘት ልንቸገር እንችላለን፤ በመሆኑም የእራሳችንን ልምዶች በመጠቀም በእኛም ሆነ በሌሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት ለማከም እርዳታ እርስ በራሳችን መሰጣጣት አለብን፡፡
  • የመሬት መንቀጥቀጥ ካደረሰው አደጋ በተጨማሪ ከመሬት መንቀጥቀጡ በኋላ በብዙ ቦታዎች ለመናድ፣ ለመውደቅ እና ለመሰበር በቋፍ የሚገኙ ብዙ ነገሮች ሊኖሩ ስለሚችሉ እንቅስቃሴያችን በሙሉ በጥንቃቄ የተሞላ መሆን አለበት፡፡ እግራችን በተለያዩ ስብርባሪዎች ሊጎዳ ስለሚችል በተቻለን አቅም ጠንካራ ሶል  ያላቸው ጫማዎችንም ማድረግ አለብን፡፡
  • በአደጋው ሰዓት ሆነ ከአደጋ በኋላ የተነሱ ከባድ እሳቶችን ለማጥፋት መሞከር የለብንም፤ ማድረግ ያለብን ከአካባቢው በቶሎ መራቅ ነው፡፡ መጀመሪያ መዳን ያለብን እኛ ነን፡፡
  • ተቀጣጣይ የሆኑ ነገሮች እንዲሁም የተለያዩ መድሃኒቶች ተበታትነው የሚገኙ ከሆነ ልናፀዳቸው ይገባል፡፡
  • የደረሰው አደጋ ከባድ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ አስከትሎ ከከተማ የሚያሰድድ ከሆነም ቤታችን ግርግዳ ወይም በር ላይ ወዴት እንደሄድን፣ የምንገኝበትን ወቅታዊ አካላዊ ብቃት እና የቤተሰቡ አባላትን ስም ዝርዝር ፅፈን መለጠፍ አለብን፡፡ ምንም አደጋ ያልደረሰብን ከሆነም እርዳታ እንደማያስፈልገን ፅፈን መለጠፍ አለብን፡፡
  • ከአደጋው በኋላ የጋዝ፣ የውኃ እና የኤሌትሪክ መስመሮች የጉዳታቸው መጠን ምንም ይሁን ምን ልንዘጋቸው ይገባል፡፡ ምክንያቱም የሚገኙበት ሁኔታ ተባብሰው የከፋ አደጋ ሊያደርሱ የሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ

ምንጭ:- መረጃ

 

 

Advertisement