ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ሁሌም ሰክቶ መጠቀም ባትሪውን ይጎዳ ይሆን…?

                                            

የላፕቶፕ ኮምፒውተር ሶኬት ሁሌም ሰክቼ መጠቀም የኮምፒውተሬን የባትሪ እድሜ ይጎዳ ይሆን? ይህ ከባትሪ ጋር ተያይዞ በኢንተርኔት ላይ በብዛት ፍለጋ የተካሄደበት ጥያቄ ነው።

የላፕቶፕ ኮምፒውተር ባትሪ ለኮምፒውተሩ ወሳኝ ከሚባሉ ክፍሎች አንዱ ነው፤ ሆኖም ግን በርካቶቻችን ስለ ኮምፒውተሩ አቅም፣ ራም እና ሲፒዩ እንጂ ስለ ባትሪ ልብ ብለን ስንገዛ አይስተዋልም።

ሆኖም ግን “ሁሌም ስጠቀም የላፕቶፕ ባትሪዬን ሰክቼ ልጠቀም ወይስ ባትሪዬ እስኪያልቅ ድረስ ከተጠቀምኩ በኋላ እንዳዲስ ሀይል እየሞላው ልጠቀም?” የሚሉ ጥያቄዎች አሁንም ቢሆን አልፎ አልፎ መነሳታቸው አልቀረም።

ይህን መመለስ ቀላል አይደለም የተባለ ሲሆን፥ ሆኖም ግን መልሱን በቀላሉ ለመረዳት ያስችለን ዘንድ ስለ ላፕቶፕ ባትሪ ያሉ እውነታዎችን እንመልከት።

የላፕቶፕ ባትሪ እውነታዎች

አብዛኛው የላፕቶፕ ኮምፒውተር ባትሪዎች “ከሊትየም አዮን” አልያም “ከሊትየም ፖለይመር” የተሰሩ ሲሆን፥ በተደጋጋዊ ያለገደብ ሀይል እንዲሞሉ ወይም ቻርጅ እንደደረጉ ተደርገው ነው የሚሰሩት።

ባትሪዎቹ ከሚያስፈልጋቸው በላይ ሀይል እንዳይወስዱ ተደርገው የተሰሩ ሲሆን፥ ይህም ባትሪው አንድ ጊዜ 100 በመቶ ሀይል ከሞላ በኋላ በራሱ ጊዜ ሀይል መውሰድ ያቆማል።

ስለዚህ ላፕቶፑን ቀኑን በሙሉ ሶኬት ላይ ሰክተን ብንጠቀም ባትሪያችንን አይጎዳም ተብሏል።

ሌላው እውነታ የላፕቶፕ ባትሪ እድሜ ለማርዘም የሚረዳን ዘዴ የሚጠቁመን ሲሆን፥ ይህም የላፕቶፕ ባትሪዎች ያለደብ በድግግሞሽ ሀይል መሞላት ወይም ቻርጅ መደረግ እንዲችሉ ተደርጉ ነው የተሰራው ይላል።

ታዲያ ባትሪያችንን አሁን አሁንም ሀይል ሞልቷል እያልን መንቀል የባትሪያችንን አቅም ሊጎዳብን ይችላል እና እዚህ ጋር ልብ ብንል መልካም ነው።

የላፕቶፕ ኮምፒውተር ባትሪ ፀር

ለላፕቶፕ ኮምፒውተር ባትሪ ጸር ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ የላፕቶፕ ኮምፒውተር ከመጠን በላይ የሆነ ሙቀት እንደሁነ ይነገራል።

ከመጠን ያለፈ የኮምፒውተር ሙቀት በተለይም የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ባትሪ እድሜ እንዲያጥር ከሚያደርጉ ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነም ይነገራል።

ለዚህም የላፕቶፓችን የሙቀት መጠን እስከ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ከሆነ ብንጠቀም ችግር የመውም የተባለ ሲሆን፥ ሙቀቱ ከዚያ የሚያልፍ ከሆነ ግን መጠቀም ማቆም ይመከራል።

አሊያም የላፕቶፓችን ባትሪ ተነቃይ ከሆነ ባትሪውን በመንቀል ቀጥታ መጠቀም የባትሪ እድሜ ለማርዘም ይረዳል ተብሏል።

ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች ላይ በመመርኮዝ ለባትሪ እድሜ እነዚህን ተግባራት መከወን

ላፕቶፑ ሀይል ወስዶ ከጨረሰ በኋላም ቢሆን ሶኬቱን አለመንቀል።
የላፕቶፕ ባትሪው የሃይል መጠን ከ40 እስከ 80 በመቶ መካከል ማድረግ።
ላፕቶፓችን ከመጠን በላይ ሙቀት እንዳይከሰትበት አየር መቆጣጠሪያ /ፋን/ እንደሚሰራ ማስተዋል።

ምንጭ:- techtalkethiopia

 

Advertisement