በጓደኛ ወይም በቤተሰባችን ላይ የፅንስ መቋረጥ ሲያጋጥም መለገስ ያለብንና የሌለብን ምክሮች

                                             

በጓደኛዎ ወይም ቤተሰብዎ የልጅ ማጣት አልያም የፅንስ መቋረጥ በሚፈጠርበት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ የስነልቦና ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በዚህ ሳምንት (በፈረንጆቹ ከ9 እስከ 15 ጥቅምት) ልጃቸውን ያጡ ወይም ፅንስ የተቋረጠባቸውን ሰዎች የሚታሰብበት ሳምንት ነው።

የፅንስ ማቋረጥ ከሚያግጥማቸው ሴቶች 95 በመቶ የሚሆኑት አጋጣሚው ከተፈጠረ በኋላ ምንም ዓይነት ድጋፍ እና ምክር እንደማያገኙ ጥናቶች አረጋግጧል። 

በጣም ትልቅ ከሚባሉት ጉዳዮች አንዱ እና ዋነኛው ደግሞ ጓደኞቻቸው ወይም የቤተሰብ አባሎቻቸው በአስከፊው ወቅት ከዚህ በፊት እንደነበሩበት ሁኔታ ያለመገኘታቸው ነው።

በተጨማሪም ቤተሰቦቻቸው ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባቸው አያውቁም ነው የተባለው።

ስለዚህ የፅንስ መቋረጥ ያጋጠማትን ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል ለመርዳት ስንፈልግ፥ ማለት ያለብን እና ማለት የሌሉብን ነጥቦች እንደሚከተለው ቀርበዋል።

1. ማለት የሌለብን

 “ቢያንስ በቀጣይ እርጉዝ መሆን እንደምትችዪ ታውቂያለሽ”

ይህ አነጋገር እርጉዝ መሆን እንደሚቻል እንጂ ወልደው በሙሉ ጊዜ ሊያሳድጉ እንደሚችሉ የሚገልፅ ባለመሆኑ ከጥቅም ይልቅ ጉዳት ስላለው ከመናገር መቆጠብ ይገባል።

ከዚህም ባለፈ አነጋገሩን የፅንስ መረጥ ያጋጠማቸው ሴቶች ወይም ልጃቸውን ያጡት በመጥፎ ሊተረጉሙት ይችላሉ።

 “እንደገና መሞከር ይቻላል”

አንድ ሴት በፅንስ ማስወረድ ሳቢያ ያጣችውን ልጅ መተካት እንደማትችል ልታስብ ስለምትችል እንዲህ ከማለት መጠንቀቅ ይመከራል።

 “ላንች መሆን ያልነበረበት ነው የሆነው” 

ይህ አባባል በሚፈጥረው የተሳሳተ ግንዛቤ ምክንያት አንድ እናት የተሳሳተ ነገር ልታስብ ትችላለች። 

በዚህ ጊዜ ማሰብ የምትችለው “ ይህ ሁሉ ለምን ይሆን? ይህ ለምን መሆን የለበትም? ለምን ለእኔ?” ወዘተ በሚል ያልሆነ ሃሳብ በማሰብ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ መድረስ ስለምትችል እንደዚህ ያለ ምክር መስጠት አያስፈልግም። 

 “ በቀጣይ ጊዜ የተሻለ ዕድል አለ” 

ይህ አገላለፅም ምንም ነገር እንዳልተከሰተ በማስመሰል የእናትን ልጅ የመውለድ ስሜት ሊጎዳ ስለሚችል ከእንደዚህ ዓይነት አነጋገር መቆጠብ አስፈላጊ ነው ሲሉ የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይመክራሉ። 

2. ማለት የሚገባን

 “ላጋጠመሽ ችግር በጣም አዝኛለሁ”

እንደዚህ አይነት አገላለፅ እርስዎ ምን ያህል ከጎኗ እንዳሉ በማወቅ ለስሜትዎ ክብደት እንድትሰጠው እና በደንብ እንድትረዳው ያደርጋል። 

 “ እኔ ከጎንሽ ስለሆንኩኝ ምን እንደሚሰማሽ ንገሪኝ”

ልጇን ያጣች ወይም ፅንስ የተቋረጠባት ሴት አንዳንድ ጊዜ ብቻዋን ከማልቀስ እና ከማሰብ ይልቅ ጉዳቷን የሚጋራላት ሰው ልትፈልግ ትችላለች። 

በዚህ ጊዜ ከጎኗ መሆንዎን የሚያረጋግጡ መልእክቶችን በስልክ በመላክ፣ ደውሎ በማነጋገር ከብቸኝነት ስሜት በማዳን ጓደኛዎን ወይም ቤተሰብዎን መደገፍ ይችላሉ። 

እንዲህ አይነት ምክር መስጠት ለጊዜው ካለችበት ስሜት እንድትወጣ ከማድረግ ባለፈ እንደገና ለመውለድ ዝግጁ እንድትሆን ያደርጋታልም ተብሏል። 

በተጨማሪም የእርስዎን ድጋፍ ሁል ጊዜ እንድታስታውሰው እና መንፈሰ ጠንካራ እንድትሆን ያግዛትል።

ምንጭ:- FBC

Advertisement