አትክልትና ፍራፍሬ ተመጋቢወች በስጋ ፋንታ የሚጠቀሟቸው ምግቦች ከፍተኛ የጨው ይዘት አላቸው

አትከልትና ፍራፍሬ ተመጋቢወች በስጋ ፋንታ የሚጠቀሟቸው ምግቦች ከፍተኛ የጨው ይዘት እንዳላቸው ተገልጿል።

በለንደን ”ኩዊይን” ሆስፒታል የልብ ጤና ፕሮፌሰር የሆኑት ግርሃም ማክገርጎር እንደተናገሩት ከምግብ ጋር የሚወሰድን የጨው መጠን በማስተካከል በልብ ህመም እና ሌሎች ተያያዥ በሽታዎች የመያዝ እድል ለመቀነስ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህን ታሳቢ በማድረግ የሚሰራው ስራ ውስን በመሆኑ ባርካታ ሰዎች ቀድሞ መከላከል ለሚቻሉ ተያያዥ በሽታዎች አንደሚጋልጡ አስገንዝበዋል።

በብሪታኒያ የስጋ ይዘት በሌላቸው 157 ምግቦች ላይ በተደረገ ጥናትም 28 በመቶ ያህሉ ብቻ ጨዋማ እንዳልሆኑ ተረጋግጧል።

በዚህም የብሪታኒያ የማህበረሰብ ጤና ድርጅት ምግቦችን የሚያቀነባብሩ ተቋማት በአስቸኳይ ማስተካክያዎችን ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል ተብሏል።

ከስጋ ነጻ የሆኑ የበርገር እና ሌሎች የተቀነባበሩ ምግቦች ከፍተኛ የጨው ይዘት እንዳላቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ተመጋቢዎቹ በዚሁ ጉዳይ ላይ ጨውን ከምግባቸው በመቀነስ ጤናን ለመበቅ እንዲችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑም ታውቋል።

ለዚህ ተግባር የተቋቋመ የብሪታኒያ ቡድን ዜጎች ከምግቦቻቸው የጨው መጠን በመቀነስ ጤናቸውን ለመጠበቅ እንዲችሉ ለማድረግ እየሰራ መሆኑም ነው የተገለጸው።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.