10ኛው የአለም ከ18 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት በኬንያ ናይሮቢ ሲጀመር ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች።
ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር ሴቶች ነው የወርቅ እና የነሃስ ሜዳልያ ያገኘችው።
ውድድሩን አበራሽ ምንስዎ በ9 ደቂቃ ከ24.62 ሰከንድ በቀዳሚነት አጠናቃለች።
ይታይሽ መኮነን ደግሞ በ9 ደቂቃ ከ28.46 ሰከንድ ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች።
ኬንያዊቷ ኢማኩሌቴ ቼፕክሩይ በ9 ደቂቃ ከ24.69 ሰከንድ አበራሽን ተከትላ ገብታለች።
ሻምፒዮናው ዛሬም ሲቀጥል በሴቶች 400 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ አትሌት ሀና አምሳሉ 6 ሰአት ከ15 ላይ ኢትዮጵያን ወክላ ትወዳደራለች።
በወንዶች 400 ሜትር ደግሞ በማጣሪያው ከምድቡ 1ኛ ሆኖ ያለፈው መልካሙ አሰፋ 6 ስአት ከ45 ሰዓት ላይ በሚካሄደው የግማሽ ፍጻሜ ውድርር ላይ ይሳተፋል።
ከሰሃራ በታች ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው በዚህ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአንድ የወርቅ እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።
ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በአንድ የወርቅ እና አንድ የብር ሜዳልያ የደረጃ ሰንጠረዡን እየመራች ነው::