ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ዲራአዝ በሚል በብዕር ስማቸው ስለ ቴዲ አፍሮ የፃፋት

                             

ይህ ጽሑፍ በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ዲራአዝ በሚል በብዕር ስማቸው በ2009 ዓ/ም እርካብ እና

መንበር በሚል ባሳተሙት መፃህፍ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ቴዲ አፍሮ በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ
[ዲራዓዝ]
በኢትዮጵያውያን ሚሊኒየም ዋዜማ ላይ ቴዲ አፍሮ በጅማ ከተማ ትልቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አቅርቦ ነበር፡፡ በወቅቱ ለጅማ
እንግዳ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ አዲሰ አበቤዎችና የተለያዩ ክልል ሰዎች በአንድ በኩል ኮንሰርቱን ለመሳተፍ በሌላም
በኩል ብዙ ብዙ የሚወራላትን ጅማ ለመጎብኘት ከተማዋን አጨናንቀዋታል፡፡
የኮንሰርቱ እለት ቴዲ አፍሮ ኮንሰርቱ ከሚካሄድበት የስፖረት ማዘውተሪያ መድረክ ላይ እንደቆመ ታዳሚው ፍቅሩን
በጩኀት፤በፉጨትና በጭብጨባ ገልጾ ጋብ እንዳለ፤ቴዲ በቀጥታ ወደሙዚቃው አልነበረም ያመራው፡፡
“እንዴት ናችሁ? “ ጩኸት
አመሰግናለሁ ” ድጋሚ ጩኸት
ሰባ ሰባት፤አንድ እንጀራ ለሰባት፤እሱም ከተገኘ ምናልባት ሌላ ጩኸት
ከእናንተ ውስጥ ከድር ሰተቴን የሚያውቅ አለ?
ለአፍታ ሰው ሁሉ ረጭ አለ፡፡ አንዳንዱ ከጎኑ ወዳለው እየዞረ ከድር ሰተቴ ማነወ እያለ ጠየቀ፡፡ የሚያውቁት በፉጨት
አጅበው የአዎንታ ድምፃቸውን አሰሙ፡፡
“…ከድር ሰተቴ ማለት” ብላቴናው ንግግሩን ቀጠለ ፡፡ “…ከድር ሰተቴ ገጣሚ ብቻ አይደለም። እኛ ግጥም የምንፅፈው
በወረቀት ላይ ነው። እሱ ግን ራሱም ግጥም ነበር። ግጥሞቹ ከአንደበቱ ጋር የተሰፉ ናቸው ። በሚፈልገው ወቅት መዝገብ
ማገላበጥ ሳይጠበቅበት በየትኛውም ርዕስ ጉዳይ ዙሪያ ቅኔውም ይዘራዋል። ልበ ብርሃኑ አያ ሙሌ (ሙሉጌታ ተስፋዬ)
የግጥም ዛር ሲወዘውዘው፤ በቃሉ የያዘውን ወረቀት ላይ እንደሚያደርግ አውቃለሁ። ከድር ሰተቴ በየትኛውም ሁኔታ ወስጥ
ስሜቱን በቅኔ የሚናገር ሰው ነው። ንግግሩም ግጥም የሆነ ምትሃተኛ የጥበብ ቀንዲል…”
የድምጻዊው ንግግ ር ፀጥ ባላው ታዳሚ ጆሮ መፍሰሱን ቀጠለ። “… እሱ ከሚታወቅባቸው ግጥሞች ሁለቱን ብቻ
ብዬላችሁ ላብቃ!”
በጭብጨባ የታጀበ ጩዂት።
ተራች ተረት ሆኖ፥ ታሪክ ተረት ተረት፤ የበላ ሲያስመልስ፤ ተበይ ወዮለት።
ጩዂት ፤ ጭብጨባና ፉጨት።
በነጭ ሲያሰምሩ ፤ ቀይ አሸበርዋቸው፤
ወጣት ሲረሽኑ ፤ አልቆ ጥይታቸው፤
ካልሆነ ወዳጅ ነው፤ መጪ ጠላታቸው።
ታላቅ ጩዂት ፤ ፉጨትና ጭብጨባ ለጥቂት ደቂቃዎች ሳይቋረጡ አስተጋቡ ።

ምንጭ፦ታዲያስ አዲስ

Advertisement