የማህንነት የህክምና አማራጭ በቻይና ባህላዊ ህክምና ዘዴ ምን ይመስላል?

                                      

ሰብለ አለሙ

በአጭሩ ለሴት ልጅ የመውለድ ችግር ከወንዱ ሊበዛባትና በተለምዶም የመውለድ ችግር የሴት ልጅ ችግር ሆኖ እንዲታይ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ለብዙ ችግር ተጋላጭ በመሆኗ ነው:: በጥቂቱ

  1. ልጅ ተቀብሎ ለዘጠኝ ወር ማስተናገድ ያለበት ማህፅኗ አመቺ ካልሆነ
  2. የማህፀኗ ቱቦ□ ከተደፈነ
  3. ስትወለድ ቁጥሩ ተወስኖ የተሰጣት በዕድሜ መግፋት ምክንያት እንቁላሏ ካለቀ: ጥራቱ ካነሰ : ጭራሽኑ አኩርታ መልቀቅ ካልቻለችና ከዛም አልፎ ስሜቷ የተረባበሸ ከሆነና ከመሳሰሉት አንዱ ምክንያት እንከን ካጋጠማት የመውለድ ዕድሏ በቀላሉ ይጠባል ::

ከዚህም አልፎ ከላይ የገለጹት ምክንያቶች በላብራቶሪ ታይቶ ከሁሉም ነፃ ትሆን ከሆነች unexplained infertility ስትባል ችግሯ እንቆቅልሽ ይሆንባታል ::ይህን ክፍተት የሚሞሉ በሰለጠነው ሀገር የተለያዩ የህክምና ዓይነቶች (  holistic medicines ) ሲኖሩ : ከነዚህም ውስጥ አንዱ የቻይና ባህላዊ ህክምና ነው::

የቻይና ባህላዊ ህክምና መሰረቱ በተለያዩ የበሽታ ዓይነቶች(pathology) ስሞች ላይ የተሞረከዘ ሳይሆን በሰውነታችን ውስጥ smooth flow of the body system ( በአማርኛ ምን እንደሚባል አላውቅም) መኖሩና አለመኖሩን የሚያመለክት ዝርዝር   ጥያቄ  በመጠየቅ ሲስተሙን ውስጥ ያለው ችግር  ማስተካከል ላይ የተሞረከዘ የሆልስቲክ  ህክምና /holistic medicine/ ዐይነት ነው::

በሰለጠነው አሜሪካና አውሮፖ አገር ህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እያገኘ በመጣ ቁጥር ህክምናውን ፈልገው የሚመጡት የታካሚዎች የፍላጎት መለያየትም በዛው መጠን እየጨመረ ነው:: ከመሃንነት ህክምና ጋር በተያያዘ አራት የተለያየ ፍላጎት ይዘው ወደ ቻይና የህክምና መሃከል ሲመጡ : ከአራቱ ሁለቱ :-

  1. መሉለሙሉ የምህራቡን Assisted Reproductive Technology( ክፍል ሁለት የፃፍኩትን ይመልከቱ) የሚለውን አማራጭ ለመሞከር ጥንዶች ወስነው ነገር ግን

1.1 ከሚሰጣት መድሀኒቶች የጎንዮሽ ጉዳት ለማገገም

1.2  ሂደቱ ( timed sex ) ከሚፈጥረው( stress)   ውጥረት ለመረጋጋት

1.3 በ አይ ቪ ፍ (IVF) ቴክኖሎጂ እንቁላል ና የወንድ ዘር ውህድ ወደማህፅኗ ከገባ በኃላ ማህፀኗ አቅፎ እንዲይዝ በማድረግ የማስወረድ አጋጣሚዋን ለመቀነስ ጎንለጎን የቻይና ህክምና ስትወስድ

  1. ሁለተኛው ዓይነት ጥንዶች ደግሞ በተቃራኒው ሙሉለሙሉ በኸርባልናበደርቅ መርፌው ብቻ ለመታከም ወስነው የሚመጡ ናቸው:: ሂደቱም የታካሚያዎና የአካሚው ሙሉ ትብብርና ትግስት ይጠይቃል::

ይህ ህክምና ከ 1-1:30 ባላነሰ ሰዓት ውስጥ የሚቆይ ሙሉ መጠይቅ በማድረግ የህክምናው እንቆቅልሽ መፍቻ መንገድ ይጀመራል ::ህክምናው በሽታ ነክ ያልሆኑ ሁለገብ ጥያቄዎችና የሙሉ ሰውነት አካሏ የሚዳስሰ ሲሆን በጥቂቱ ስለወር አበባዋ ዝርዝር ጥያቄ: በወር አበባዋ ጊዜ ና በፊት የሚሰማት ስሜቶች : አጠቃላይ ስሜቶቿ : ስለምግብ መፍጫ አከሏ: ሰገራ ሽንት  የመሳሰሉት  ሲሆኑ  ህክምናው በራሱ የህክምና ሳይንስ ላይ ተመስርቶ ስለሚያክም በአብዛሃኛው ላብራቶሪ ሊያገኘው ያልቻለውን ‘ unexplained infertility ‘ የሚል የህክምና ውጤት የተሰጣትን ሴትን( ጥንዶች) ጨምሮ ለማከም ይችላል::

ሂደቱ እንደበሽታው መቆየትና ውስብስብነት በትንሹ ሴት ልጅ ለ3 ወር ህክምናውን እንድትከታተል ሲትመከር ከአንድ አመት የበለጠ ጊዜ የሚፈጅበት ወቅትም ሊከሰት ይችላል :: ይህ የሚሆንበት ምክንያትም ህክምናው ትኩረቱ ተፈጥሮሃዊዉን የሰውነት ሂደት ስለሚከተልና የህክምናው ዋና ትኩረት የመውለድ ችግር መንስሄ የሆኑትን እንከኖችን በማስተካከል ተፈጥሮሃዊውን ሂደት አንዲቀጥል በማድረግ ላይ ስለሚሰራ ነው::

መጀመሪያ ጥንዶች ሙሉ የላብራቶሪ ውጤታቸውን ይዘው እንዲመጡ ይመከራሉ:: ይህም የመካንነት ችግር የሴቷ ወይም የወንዱ ለመሆኑ መልስ ለማግኘትና በዚህ ህክምና መፍትሔ ሊያገኙ የሚያስችላቸው ይሁን ወይንም አይሁን በግዜው ውሳኔ ለማግኘት ይጠቅማል::

የህክምናው ዋንኛ ተግባሮች

  1. የመሃፅን ቱቦ በከፊል ተዘግቶ ከሆነ እንዲከፈት ማድረግ ( ለዚህ የሚሰጡ ኸርባሎች በጣም ጠንካራ ስለሆኑ ጥንዶች ከእርግዝና ሙከራ ለጊዜው እንዲያቆሙና ት ቴራፒው ሙሉለሙሉ በአጭር ግዜ ውጤት እዲያገኙ እንዲፈቅዱ ይመከራሉ::
  2. ሆርሞኗ ከተዛባ ማስተካከል
  3. እጢዎች ካሉ መጠናቸው በመቀነስ ለእርግዝና መሰናክል የሆነውን አጋጣሚ በከፍተኛ መጠን መቀነስ በጥቂቱ ሲሆኑ የህክምናው አንዱ አካል የሆኑት የምግብና ውጥረት መቀነሻ መንገዶች ከሆኑት እንደ ሜድቴሽንና ቺኩንግ ስሜት ማረጋጊያ እንቅስቃሴዎች እሷም ሆነች ባላቤቷ እንዲሞክሩ ይመከራሉ::

የወንድ ልጅ ችግር ማከሚያ ሂደት ተመሳሳይ ሲሆን ከሴቶ ትንሽ ቀለል ይላል::

በምህራቡ ሀገር ላለፉት ጥቂት ዓመታት የሁለቱ የህክምና ዘዴዎች በአንድ ጣሪያ ስር ባይሰሩም ታካሚዎች ሁለቱን የህክምና አማራጮች በማቀራረባቸው አብሮ የመስራቱ መንፈስ ከሞላጎደል ጥሩ ነው::

በሚቀጥለውና የመጨረሻው ፁሁፌ ላይ ለችግሩ መንስሄ እና መባባስ ምክንያቶች ናቸው የሚባሉትን አኗኗሪያዊና እና አከባቢያዊ ( life style and environmental factors ) ተፅህኖችን በአጭሩ እጠቅሳለው::

** ለአንባቢዎች : በተከታታይ በፃፍኩት ፁሁፌ ላይ ለተፈጠረው የቃላት ግድፈቶች ይቅርታ እየጠየኩ : በአለፈው ፁሁፌ ላይ የመሃፀን መደፈን ተብሎ የተነበበውን የመሃፀን ቱቦ መደፈን ተብሎ እንዲነበብ ከይቅርታ ጋር እጠይቃለው::

ምንጭ፦ Amhara Mass Media Agency

Advertisement