አብዛወኛውን ጊዜ ከሰውነት ውፍረት ጋር ተያይዞ በርካታ ሰዎች ለጠና እና ማህበራዊ ህይወት መቃወስ ሲጋለጡ ይስተዋላል።
ታዲያ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ቀውስ ለመውጣት በአካል ብቃት እንቅስቃሴ አሊያም በቀዶ ህክምና የሰውነታቸውን ክብደት ለመቀነስ ሲተጉ ይስተዋላል።
ተመራማሪዎች አዲስ ባወጡት ጥናት ደግሞ የሰውነትን ክብደት በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ ጥቅም እንዳለው ጉዳቶችም አሉት ይላሉ።
እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት ወይም ውፍረትን በቀዶ ህክምና ማስወገድ በፍቅር ግንኙነት ላይ ጉዳቶች እና ጠቀሜታዎች እንዳለው ይገልጿሉ።
በቀዶ ህክምና ውፍረትን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ በፍቅር ግንኙነት ላይ ተፅዕኖ እንዳለው ነው ተመራማሪዎቹ የሚናገሩት።
ከተካሄዱት ሁለት ጥናቶች መካከል አንድ ጥናት ከቀዶ ጥገና በሃላ የሚከሰት የውፍረት መቀነስ በከፍተኛ ሁኔታ ከፍቺ ጋር እንደሚያያዝ ነው ያረጋገጠው።
ሌላኛው ጥናት ደግሞ ግንኙነት ያልፈጠሩ ሰዎች የፍቅር ህይወት እና ትዳር እንዲጀምሩ እንደሚያስችል አመልክቷል።
በጥናት ክብደት ለመቀነስ የተካሄዱ ቀዶ ጥገናዎች በህይወታቸው ላይ መሻሻል እንደታየ ተመልክቷል።
እንደ ጥናቱ በተሻለ ደረጃ ውፍረታቸውን የሚቀንሱ ሰዎች የደም ግፊትና ስኳር በሽታ ተጋላጭነታቸው ይቀንሳል ተብሏል።
በመሆኑም በአካል እና በእዕምሮ ደረጃቸው ከፍተኛ ለውጥን የሚያመጡ በመሆኑ በራስ መተማን እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል።
እንዲሁም በውፍርት የተጠቁ ሰዎች ተያያዥ የጤና ሁኔታዎች ለመቆጣጠር ውፍረትን መቀነስ ጥሩ ህክምና መሆኑ ነው የተገለፀው።
ይህም ተቀባይነት በማግኘቱ በፈረንጆቹ 2013 400 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከልክ ያለፈ የሰውነት ውፍረት መቀነሻ ቀዶ ጥገና ህክምና ማድረጋቸው ታውቋል።
ነገር ግን በዚህ ጥናት መሰረት ህክምናው ህይወት ማሻሻል ቢችልም ለሱስ አጋላጭ ሆኖ እንደተገኘ ይነገራል።
ይህ ጥናት በ10 ዓመት ውስጥ ቀዶ ጥገና 2 ሺህ ሰዎች እና ቀዶ ጥገና ያላከናወኑ 1 ሺህ 900 ሰዎችን ያሰተፈ መሆኑ ታውቋል።
እንዲሁም በሶስት ዓመታት ውስጥ የጨጓራ ቀዶ ጥገና ያከናወኑ 29 ሺህ ሰዎች ማሰተፉ ተነግሯል።
ምንጭ:- ኤፍ ቢ ሲ(FBC)