የተልባ የጤና ጥቅሞች (Flax Seeds)

ተልባ ጥንታዊ የእህል አይነት ሲሆን፣ በሰውልጅ የማዕድ ገበታ ላይ ለበርካታ ሺ አመታት ይታወቃል።የሕክምና አባት ተብሎ የሚታወቀው ሂፖክራተስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ650 ተልባን ለሆድ ሕመም ማስታገሻነት ይጠቀመው ነበር።

በ8ኛው ክፍለ ዘመን ንጉሥ ቻርልማኝ የተልባን ጠቀሜታ በመረዳቱ ሕዝቡ በቋሚነት እንዲመገበው ለማድረግ ህጎችን እና ደንቦችን አውጥቶ ነበር። የዘመናዊው ዓለም ሳይንቲስቶችና የስነ_ምግብ ባለሙያዎችም ከበርካታ ዘመናት በኋላ፣ ይህንኑ የተልባን የጤና ጠቀሜታ አረጋግጠዋል።

አንዳንዶች ተልባን በምድር ላይ ከሚገኙ ተክሎች ሁሉ እጅግ ኃይለኛው ነው ይሉታል። የልብ በሽታን፣ ካንሰርን፣ የልብ ድካምን እና የስኳር በሽታን መከላከል እንደሚችል አንዳንድ ምልክቶች ታይተዋል። ተልባ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ3,000 ዓመተዓለም በባቢሎን ይመረት ነበር ሲል የካናዳ የተልባ ካውንስ ድርጅት(The Flax Council of Canada) ይገልጻል። በአሁኑ ወቅት ተልባ በበርካታ የምግብ ዓይነቶች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ በ2006 ብቻ ተልባን እንደ ንጥረ_ነገር የተጠቀሙ 75 ምርቶች ለገበያ በቅተዋል።

ተልባ ካሉት ጠቀሜታዎች በጥቂቱ

ተልባ ኮሌስትሮልን ይከላከላል:- ተልባን መመገብ የኮሌስትሮል መጠንን ይቀንሳል። ይህም መጥፎ የሚባለውን LDL ኮሌስትሮልን እና triglycerides የተሰኘውን ይጨምራል። በርካታ ጥናቶች በየዕለቱ ተልባን መመገብ ጥሩ ውጤት ያስገኛል ይላሉ።

ተልባ እና የስኳር በሽታ!

የሥነ_ምግብ ባለሙያዎች የስኳር በሽተኞች ተልባን በየዕለቱ እንዲመገቡ ይመክራሉ። በውስጡ የያዛቸው ኦሜጋ_3፣ fat እና ፋይበር ስኳርን በመዋጋት በኩል ከፍተኛ አስታውፆ አላቸው። በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የተካሄደ ጥናት ላይ ተሳትፈው፣ ከተልባ የተሰራ ዳቦ የበሉ የስኳር በሽተኞች የደም የስኳር መጠናቸው ዳቦውን ከመብላታቸው በፊት ከነበረበት መጠን በ28% ቀንሶ ተገኝቷል። በተቃራኒው ከስንዴ ዱቄት ብቻ የተሰራ ዳቦ የተመገቡ ሌሎች በሽተኞች ላይ ግን ምንም አይነት ለውጥ ሳይገኝ ቀርቷል።

ካንሰርን ይከላከላል!!

Lignans የተሰኘ ንጥረ ነገር ተልባ ውስጥ በከፍተኛ መጠን ይገኛል። ከሌሎች ተክሎች 800 ጊዜ እጥፍ በሆነ መጠን ነው ተልባ ውስጥ ያለው። ይህ ንጥረ ነገር ተፈጥሯዊ የካንሰር ተከላካይ ውህዶችን ይዟል። የአሜሪካ ብሔራዊ የካንሰር ኢንስቲትዩት ልዩ ትኩረት(Special Study) ሊሰጣቸው ይገባል ሲል ከዘረዘራቸው ስድስት ምግቦች ተልባ አንዱ ነው። የያዘው ከፍተኛ ፋይበር የትልቁ አንጀት ካንሰርን (Colon Cancer)ለመከላከል ይጠቅማል። አንድ ጥናት በፋይበር የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ በትልቁ የአንጀት ካንሰር የመያዝዕድልን ይቀንሳሉ ብሏል። ተልባ በፋይበር፣ በ_Lignans,alpha linolenic acid የበለፀገ በመሆኑ በተለይ የጡት እና የትልቁ አንጀት ካንሰርን ይከላከላል።

ተልባ እና የሆድ ድርቀት!

ተልባ Soluble እና insoluble የሚባሉትን ሁለት የፋይበር አይነቶች ይዟል። 30 ግራም ተልባ ለአንድ እለት የሚበቃን ያህል ፋይበር ያስገኝልናል። በያዘው ከፍተኛ insoluble ፋይበር የተነሳ የሆዳችንን እንቅስቃሴ ጤናማ እንዲሆን ያደርጋል። ፋይበር ሰውነታችንን በቂ ውሃ እንዲይዝም ይረዳል። በዚህ ምክንያትም ድርቀት እንዳያስቸግረን የሚያደርግ ነው።

Advertisement