ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም

አዲስ አበባ፣ ህዳር 22፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከተፈላጊ የህወሓት ጁንታ አባላት አንዷ የሆኑት ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም በህውሓት ከፍተኛ አመራርነት፣ በመንግስት ከፍተኛ ሃላፊነት እንዲሁም በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት አገልግለዋል።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም የህወሓት ጁንታው ጥቅም ይሻለኛል ብለው ወደ መቀሌ የሸሹ ሲሆን ሾፌራቸው ግን የመንግሥትን ንብረት ለጁንታው አልሰጥም ብሎ ከመቀሌ ወደ አዲስ አበባ ይዞት መምጣቱ ይታወሳል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ በሰላማዊ መንገድ እንደ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ሌሎችም የህወሓት አመራሮች እጅ እንዲሰጡ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል።

ተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ምንጭ: ፋና ቢሲ

Advertisement