የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር በብዙ ሰዎች ላይ የሚከሰት የህመም ዓይነት ነው ፡፡ በተለይ እድሜያቸው ከ 50 እስከ 60 ዓመት የሆናቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የመከሰት እድሉ ሰፊ ነው ፡፡

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር መነሻ ምክንያቶች

-የቀዳማዊ የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር 60 በመቶ ያህል የሚሆነው የሚመጣው በቤተሰብ የዘር ሐረግ መሃል ሊኖር በሚችል ተመሳሳይ ችግር ምክንያት ነው ፡፡
– የመገጣጠሚያ አካላት በተፈጥሮ ችግር ኖሮባቸው መፈጠር 
– የስኳር ህመም
– የሪህ ህመም
– በነዚህ አካባቢዎች የተፈጠረ አደጋ 
– የሠውነት ክብደት መጨመር

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግር መከሰት ምልክቶች

– ጡንቻዎችን የመለብለብ ስሜት መኖር
– በመገጣጠሚያዎች አካባቢ በተለይ በታፈነና በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታዎች ወቅት የሚኖር የህመም ስሜት
– የጡንቻዎች መኮማተር 
– በችግሩ የተጠቁ አካባቢዎች እብጠት ማሳየት እና የህመም ስሜት 
– በቁርጭምጭሚት መጋጠሚያዎች አካባቢ የፈሳሽ መጠራቀም

የአጥንት መገጣጠሚያዎች ችግርን ለመቆጣጠር የሚረዱ መንገዶች

– የሠውነት ክብደትን መቆጣጠር
– የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን ማድረግ

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.