አስፕሪን የተባለው መድኃኒት የትልቁ አንጀት ካንሰር በሽታን ይከላከላል

መድሃኒቱ የትልቁ አንጀት ካንሰር በሽታን መከላከል የሚያስችል ቢሆንም÷ የመድሃኒቱ ተጠቃሚዎች ውስን መሆናቸው ተነግሯል፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በትልቁ አንጀት ላይ የህመም ስሜት የሌላቸው ነጠብጣቦች የሚከሰቱ ሲሆን÷ እነዚህ ነጠብጣቦች የትልቁን አንጀት የካንሰር ተጋለጭነት እንደሚጨምሩ ታውቋል፡፡

ክስተቱ በምርመራ የሚለይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ ችግሩ የተከሰተባቸው ሰዎች ሌሎች መድሃኒቶችን የማይወስዱ ከሆነ መጠኑ ዝቀተኛ የሆነ አስፕሪን እንዲወስዱ የአሜሪካው የካንሰር መከላከል ግብረ ኃይል ይፈቅዳል፡፡

አስፕሪን የተባለው መድኃኒት የትልቁ አንጀት ካንሰርን 40 በመቶ ያህል በመካላከል ትልቁ አንጀት ላይ የሚወጡ ነጠብጣቦችንም ለማስወገድ እንደሚያስችልም ነው የተነገረው፡፡

የአትላንቲክ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ከ2013 እስከ 2017 ዓ.ም ባደረጉት ጥናት በትልቁ  አንጀት ላይ ነጠብጣቦች ወጥቶባቸው አስፕሪን የተባለውን መድሃኒት እንዲወስዱ ከታዘዙት 85 ሰዎች መካከል 43 በመቶ ያህሉ ብቻ መድኃኒቱን በትክክል መውሰዳቸውን ተረጋግጧል፡፡

የዚህን በሽታ ተጋላጭነት ለመቀነስ የትልቁ እንጀት የካንሰር ቅድመ ምርመራ ማድረግ፣ የአካል ብቃት እንቀስቃሴ መስራት፣ አመጋገብን ማስተከል ጠቃሚ መሆኑን ተማራማሪዎቹ ይናገራሉ፡፡

በሽታው ከተከሰተ በኋላም በሀኪም የሚታዘዙ መድሃኒቶችን በትክክል መወሰድ ጤናን ለማስተካከልና እድሜን ለማራዘም እንደሚያስችሉ ተማራማሪዎቹ ይመክራሉ፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

3 Comments

Comments are closed.