ለብብት መትቆር መፍትሄዎች

ለብብት መጥቆር መፍትሄ ለመፈለግ የሚረዱ ዘዴዎች

1.ቤኪንግ ሶዳ ፡ – ሁለት የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ሶዳ በውሃ ወፈር አድርገን መበጥበጥ እና ብብታችንን መቀባት 
– ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ያህል መቆየት ከዛም ብብታችንን ማጽዳት በሳምንት 2 ጊዜ ብንጠቀመው ይመረጣል

2. ሎሚ ፡ – ሎሚ በሁለት ቆርጠን ብብታችንን በሎሚው ማሸት 
-ከዚያም በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ( ብብታችንን ከላጨን በኋላ ወድያው ከተቀባን ሊያቃጥለን ስለሚችል መጠንቀቅ ይኖርብናል) 
– በሳምንት 4 ጊዜ ብንጠቀም የተሻለ ለውጥ ያገኛል

3. ኪያር ፡ – ኪያር በስሱ እየቆራረጥን የጠቆረ የብብት ቆዳችንን መቀባት ከዚያም ለ 30 ደቂቃ አቆይተን በመታጠብ ብብታችንን ማጽዳት

4 . ድንች ፡ – ድንች በስሱ እየቆረጥን የጥረቆረ የብብታችንን ክፍል ማሸት ወይም የድንች ጭማቂ ተቀብተን ለ 15 ደቂቃ በማቆየት በቀዝቃዛ ውሃ በመታጠብ የጠቆረ ብብታችንን ማጽዳት

5 . የጥርስ ሳሙና ፡ – አንድ ማንኪያ የጥርስ ሳሙና በጣታችን የብብታችንን ቆዳ መቀባት እና ለ 5 ደቂቃ ማቆየት ከዚያ በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ወይም ሻወር ከመግባታችን ከ 5 ደቂቃ በፊት መቀባት እና መለቅለቅ

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.